አዲስ ስደተኛ በኖርዌይ

አዲስ ስደተኛ በኖርዌይ

ኖርዌይ ውስጥ ለመኖር የሚፈልጉ የዉጭ ሃገር ዜጎች የመኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት ህጋዊ የሆነ ምክንያት ሊኖራቸው ይገባል። የአንድ ሰው መብትና ግዴታዎች የሚወሰኑት በያዘው የመኖሪያ ፈቃድ ዓይነት መሰረት ነው። ስለዚህ ሁሉም ሰዉ የሚመለከተዉን ህግ ጠንቅቆ ማወቅ ይኖርበታል።
ኖርዌይ ውስጥ የሚኖር ማንኛውም ሰው የሃገሪቱን ህጐችና ደንቦች በደንብ የማወቅ ግዴታ አለበት። በሚመለከተዉ የመንግስት አካል በሚጠየቅበት ጊዜም ትክክለኛውን መረጃ የመስጠት ግዴታ አለበት።

መረጃ

በኖርዌይ የሚኖሩ ሁሉ ብዙ መብትና ግዴታ አለባቸው።

ይህም ማለት ሁሉም ልጆች የመማር መብት አላቸው፣ እንዲሁም ሁሉም ሀኪም ቤት የመታከም መብት አላቸው። የሚሰሩ ሁሉ ቀረጥ የመክፈል ግዳጅ አለባቸው። የዓመታዊ ገቢ መግለጫ ስናስገባ ትክክለኛ መረጃ የመስጠት ግዳጅ አለብን። በዚህ ድህረ ገፅ ላይ ከሁሉም ዜጎች የሚጠበቀውን በተለያዩ ርእሶች ስር ማንበብ ይችላሉ።

ሥርዓቱ የተመሰረተው በመተማመን ላይ ነው

ዜጎች ትክክለኛውን መረጃ እንደሚሰጡና ህግን እንደምያከብሩ ባለስልጣናት ይተማመናሉ። የኖርዊጂያን ስርዓት የተመሰረተው በዚህ መሰረት ላይ ነው። የቁጥጥር ዘዴዎች ቢኖሩም ናሙና ብቻ ነው የሚታየው። ስያስጭበረብሩ የሚያዙ ሰዎች የተለያዩ ቅጣት ይጠብቃቸዋል። ይህም የገንዘብ ቅጣት፣ እስር፣ የህዝብ አገልግሎት ቅጣት የመሳሰሉት ሊሆን ይችላል።