አዲስ ስደተኛ በኖርዌይ

የተለያዩ የመኖሪያ ፍቃድ አይነቶች

ኖርዌይ ውስጥ ለሚኖሩ የውጭ ሃገር ሰዎች የሚሰጡ የተለያዩ የመኖሪያ ፈቃድ ዓይነቶች አሉ። ከእነዚህም ውስጥ ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡-

    • የአውሮፓ ህብረት (EU) ፣ የአውሮፓ ኢኮኖሚያዊ ቀጠና (EEA) እንዲሁም የአውሮፓ ነፃ ንግድ ማህበር (EFTA) አባል አገራት ዜጐች ኖርዌይ ውስጥ የመኖር መብት አላቸው። የእነዚህ EU / EEA / EFTA አገራት ዜጐች የመኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት ማመልከት አይጠበቅባቸውም። በማመልከት ፈንታ በቀጥታ በኢንተርኔት ከተመዘገቡ በኋላ ለፖሊስ በአካል ቀርበው ካሳወቁ በቂ ነው።
    • በከባድ ሰብዓዊ ርህራሄ ወይም ከኖርዌይ ጋር ባለ ትስስር (ሰብዓዊ ምክንያት) ለስደተኞች የሚሰጥ የመኖሪያ ፈቃድ በሃገሩ መንግስት የተሳደደ ወይም የመሳደድ ስጋት ያለበት ወይም ኢ-ሰብዓዊ አያያዝ ያጋጠመው ሰው ኖርዌይ ውስጥ ከለላ (ጥገኝነት) መጠየቅ ይችላል። ስደተኛው የከለላ ጥያቄውን ለፖሊስ በአካል ተገኝቶ ማቅረብ አለበት። ጥያቄውን አይቶ የሚያየው አካል የውጭ ሃገር ዜጎች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት (UDI) ነው። አንዳንድ ስደተኞች በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እርዳታ ቀጥታ ወደ ኖርዌይ ይመጣሉ።
    • ኖርዌይ ውስጥ ቤተሰብ ያለው ሰው ወይም ኖርዌይ ውስጥ ከሚኖር ሰው ጋር ቤተሰብ መመስረት የሚፈልግ ሰው የቤተሰባዊ ፍልሰት ፈቃድ ለማግኘት ማመልከት ይችላል። ኖርዌይ ዉስጥ ያለዉ የቤተሰብ አባል አንዳንድ መስፈርቶችን ማሟላት ይጠበቅበታል። ከእነዚህም ውስጥ የመኖሪያ ቤት ሊኖረውና የሚመጣዉን ቤተሰብ መጦር መቻል አለበት። ማመልከቻዉ በአብዛኛው የሚቀርበው ውጭ ሃገር በሚገኝ የኖርዌይ ኤምባሲ ነው።
    • በቤተሰብ አባላት መካከል ጥቃት ሲከሰት ወይም በደል ሲደርስ የጥቃቱ ሰለባ የሆነው ሰው የመኖሪያ ፈቃድ ሊያገኝ ይችላል። በትዳር ግንኙነት ውስጥ ጥቃት ወይም በደል ሲደርስ፣ የግዳጅ ጋብቻ ሲያጋጥም እንዲሁም ትዳር ከፈረሰ በኋላ ወደ ሃገራቸው ለመመለስ ፈልገው በተለያዩ ማህበራዊና ባህላዊ ምክንያቶች መመለስ የማይችሉ ሰዎች ለብቻቸው የመኖሪያ ፈቃድ ማግኘት ይችላሉ። ይህ ልጆቻቸዉንም ጭምር ይመለከታል።
    • የሥራ መኖሪያ ፈቃድኖርዌይ ውስጥ ሥራ መሥራት ለሚሹ የውጭ ሃገር ሰዎች የሚሰጣቸዉ የተለያዩ የመኖሪያ ፈቃድ ዓይነቶች አሉ።

 

መረጃ

የመኖሪያ ፍቃድ

በአንድ አገር የመኖር ፍቃድን በተመለከተ የተያዩ አገሮች የራሳቸው የሆነ ህግ አላቸው። ማን የመኖሪያ ፍቃድ እንደሚያገኝ የሚወስኑት ባለሥልጣናት ናቸው።

በሚኖሩበት አገር ውስጥ ህጋዊ መኖሪያ ፈቃድ እንድያገኙ ሁኔታዎችን ማስተካከል የእያንዳንዱ ሰው ግዳጅ ነው። በኖርዌይ ውስጥ ያሉ የውጪ ዜጎችም ለመኖሪያ ፍቃድ ማመልከትና አስፈላጊ ሆኖ ስገኝ ማሳደስ ግዳጅ አለባቸው።