አዲስ ስደተኛ በኖርዌይ

የኖርዊጂያን ቋንቋ ትምህርት

“የኖርዌይኛ

የኖርዌይኛ ቋንቋና የህብረተሰብ ዕዉቀት ትምህርት ላይ የመሳተፍ መብትና ግዴታ፡-

አንዳንድ ስደተኖች የኖርዌይኛ ቋንቋና የህብረተሰብ ዕዉቀት ትምህርት የመውሰድ መብትና ግዴታ አላቸው።
ይህ የሚመለከታቸዉ፡-

 • ስደተኞችን
 • በሰብዓዊ ርህራሄ ምክንያት የመኖሪያ ፈቃድ ያገኙ ሰዎችን
 • የጅምላ ከለላ የተሰጣቸው ሰዎችን
 • ከዚህ በላይ የተጠቀሱት ፍልሰተኞች የቤተሰብ አባል በመሆናቸው ፍቃድ የተሰጣቸው (የቤተሰባዊ ፍልሰት ፈቃድ)
 • የኖርዌያዊ ወይም የኖርዲክ ዜጋ ቤተሰብ አባል በመሆናቸዉ የመኖሪያ ፈቃድ ያገኙ ሰዎችን (የቤተሰባዊ ፍልሰት ፈቃድ)
 • ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ያለው ሰው ቤተሰብ አባል በመሆናቸዉ የመኖሪያ ፈቃድ ያገኙ ሰዎችን (የቤተሰባዊ ፍልሰት ፍቃድ)

የኖርዌይኛ ቋንቋ ትምህርት የመከታተል መብትና ግዴታ የሚመለከተው ዕድሜያቸው ከ16 እስከ 67 ዓመታት ለሆኑት ብቻ ነው። መብቱ ትምህርቱን በነፃ የማግኘት መብት ሲሆን፣ ግዴታዉ ደግሞ ተሳታፊዎች ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ (ወይም ዜግነት) ለማግኘት የ600 ሰዓታት ሥልጠና የመከታተል ግዴታ ነዉ። ከእነዚህ ሰዓታት ውስጥ ለ50 ሰዓታት ያክል ተሳታፊዉ የኖርዌይን የህብረተሰብ ዕዉቀት ትምህርት በሚረዳዉ ቋንቋ መማር አለበት። ለተጨማሪ ሰዓታት ትምህርት ማግኘት የሚቻልበት ሁኔታም አለ። እነዚህን ሰዓታት እንደ አስፈላጊነቱ የሚመድበዉ ወረዳዉ (ኮሚዩነው) ነዉ። ይሁን እንጂ ጠቅላላው የትምህርት ሰዓት ከ3000 ሰዓታት በላይ ሊሆን አይችልም።

የኖርዌይኛ ቋንቋና የህብረተሰብ ዕዉቀት ትምህርት የመከታተል ግዴታ

አንዳንድ ፍልሰተኞች ትምህርቱን በነፃ የማግኘት መብት የላቸዉም። ነገር ግን ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት ከፈለጉ ለ300 ሰዓታት ያህል የኖርዌይኛ ቋንቋና የህብረተሰብ ዕዉቀት ትምህርት ተከታትለው የማጠናቀቅ ግዴታ አለባቸው። ይህ የሚመለከታቸው የሚከተሉትን ነው፡-

 • ከአውሮፓ ኢኮኖሚያዊ ቀጠና EØS ወይም ከአውሮፓ ነፃ ንግድ ማህበር EFTA አባላት ካልሆኑ ሀገራት ለሚመጡ ፍልሰተኛ ሠራተኞች
 • ከአውሮፓ ኢኮኖሚያዊ ቀጠና EØS ወይም ከአውሮፓ ነፃ ንግድ ማህበር EFTA አባላት ካልሆኑ ሀገራት የመጡ ፍልሰተኛ ሠራተኞች ቤተሰብ አባል ስለሆኑ የመኖርያ ፍቃድ የተሰጣቸው ሰዎች

የኖርዌይኛ ቋንቋና የህብረተሰብ ዕዉቀት ትምህርት መብትም ሆነ ግዴታ የሌለባቸው

አንዳንድ ፍልሰተኞች የኖርዌይኛ ቋንቋ ትምህርት እና የህብረተሰብ ዕዉቀት ትምህርት ላይ የመሳተፍ መብትም ሆነ ግዴታ የላቸውም። ይህ የሚመለከተው፡-

 • ተማሪዎችን
 • ኦፔር (የቤት ሠራተኞች ማለትም ከኖርዌይ ቤተሰብ ጋር አብረው በመኖር ቋንቋውን የሚማሩ የውጭ ሃገር ወጣት ሴቶች ሲሆኑ፣ የቤት ውስጥ ሥራ በመሥራትና ልጆች በመጠበቅ ያገለግላሉ። ለዚህም ምግብ፣ መኝታና መጠነኛ ክፍያ ያገኛሉ)።
 • የኖርዲክ ዜግነት ያላቸዉ ሰዎች
 • በአውሮፓ ነፃ ንግድ ማህበርና በአውሮፓ የኢኮኖሚ ቀጠና ደንቦች መሠረት የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ሰዎች

መረጃ

የኖርዊጂያን ቋንቋ ኮርስ

በኖርዌይ የሚኖሩ ሁሉ ኖርዊጂያን ቋንቋ መናገርና መረዳት ይኖርበታል። የኖርዊጂያን ማህበረሰብ የሚጠብቀው ሁሉም ሰው በማህበረሰቡ ውስጥ መሳተፍንና በአብዛኛው ሰው ወደ ሥራ ተሰማርቶ ራስን መርዳት እንድችል ነው። በአብዛኛው ወረዳዎች የኖርዊጂያን ቋንቋ ትምህርት የሚሰጡ ሲሆን ሌሎችም ብዙ የግል የቋንቋ መማሪያዎች አሉ። አንዳንድ ስደተኞች ከወረዳው ነፃ የቋንቋ ትምህርት የምያገኙ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ ከፍለው መማር አለባቸው። ይህም በመኖሪያ ፍቃድ ዓይነት ላይ የተመረኮዘ ነው።