አዲስ ስደተኛ በኖርዌይ

የአገር ማላመጃ ፕሮግራም


ኖርዌይ የሚገቡ አዳዲስ ፍልሰተኞች የተሻሉ ዕድሎች እንዲገጥማቸዉ ለማድረግ የመሰናድዖ መርሀ ግብር ተሳታፊ ይሆናሉ። ይህ መርሀ ግብር አዲስ ፍልሰተኞች ከኖርዌይ ህብረተሰብ ጋር የሚያስተዋውቅ ሲሆን መርሀ ግብሩን የማዘጋጀት ኃላፊነቱ የወረዳዉ (ኮሚዩነ) ነው።
የመሰናድዖ መርሀ ግብሩ ዓላማ ፍልሰተኞች በሥራና በማህበራዊ ህይወት የተሻለ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ዕድል መፍጠር ነዉ። ዓላማው በገንዘብ አቅም ራሳቸዉን እንዲችሉ ማድረግ ነው።

አንዳንድ ፍልሰተኞች የመሰናድዖ መርሀ ግብሩ ላይ የመሳተፍ መብትና ግዴታ አላቸው። ነገር ግን ግዴታው ለሁሉም አይደለም። ይህ የሚወሰነዉ በተሰጣቸው የመኖሪያ ፈቃድ መሠረት ነዉ።
በዚህ የመሰናድዖ መርሀ ግብር ላይ የመሳተፍ መብትና ግዴታ ያላቸው የሚከተሉት ናቸው።

  • ስደተኞች
  • በሰብአዊ ርህራሄ የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ሰዎች
  • ከላይ ከተጠቀሱት ሁለቱ ቡድኖች ጋር በቤተሰብነት የተቀላቀለ ሰው
  • በትዳር ግንኙነት ውስጥ በራስ ወይም በልጅ ላይ በደረሰ ጥቃት፣ የበደል እና የግዴታ ጋብቻ ሰለባ በመሆናቸዉ ምክንያት፣ ወይም ከትዳር መፍረስ በኋላ ወደ ሃገራቸው ለመመለስ ፈልገው በተለያዩ ማህበራዊና ባህላዊ ምክንያቶች መመለስ ስላልቻሉ ብቻ የመኖሪያ ፈቃድ ላገኙ ሰዎች

 

መረጃ

የማላመጃ ፕሮግራም የሚረዳው

  • ስደተኞች በሥራና በማህበራዊ ኑሮ እንዲሳተፉ እድል ይፈጥራል
  • የስደተኞችን በኢኮኖሚ ራስን መቻልን ያጠናክራል
  • በኖርዊጂያን ቋንቋ መሰረታዊ እውቀት እንዲያገኙ ይረዳል
  • ስለ ኖርዊጂያን ማህበረሰብ መሰረት ይሰጣል