አዲስ ስደተኛ በኖርዌይ

በሥራ አለምና በማህበራዊ ህይወት ውስጥ እንዴት መግባትና በንቃት መሳተፍ ይቻላል?

“የመጋዘን “የሸቀጣሸቀጦች መደብር ሠራተኛ”

ለኖርዌይ አዲስ የሆነ ሰው ብዙ ነገሮች አዲስና እንግዳ ይሆኑበታል። ፍልሰተኞች በፍጥነት ከአካባቢው ጋር መላመድና በመጨረሻም የኖርዌይ ህብረተሰብ አባል ነኝ የሚል ስሜት ማዳበር መቻላቸዉ ለራሳቸዉና ለህብረተሰቡ በጣም ጠቃሚ ነው።

በጣም አስፈላጊው ማንም ሊያደርገው የሚችለው ነገር ቢኖር የኖርዌይኛ ቋንቋን መማር ነው። የቋንቋ ትምህርቱ በተለያዩ ዘዴዎችና መድረኮች ይሰጣል። አብዛኛዎቹ ፍልሰተኞች ቋንቋውን መማራቸው ብዙ ይጠቅማቸዋል። ቋንቋዉ የሚዘወተርባቸው ቦታዎችን ፈልጎ ማግኘት አስፈላጊ ነው። ይህም በሥራ ቦታ፣ በተደራጁ የመዝናኛ እንቅስቃሴዎችና በግል ህይወት ውስጥ ሊሆን ይችላል። አንዳንድ ሰዎች በቴሌቪዥን የልጆች መርሀ ግብሮችን፣ዜና ወይም የጽሁፍ የተደገፉ መርሀ ግብሮችን በመከታተል ቋንቋውን በደንብ ይማራሉ።

የኖርዌይኛ ቋንቋ ትምህርት መርሀ ግብር ዉስጥ ተግባራዊ የቋንቋ ልምምድ የማድረግ እድል ይኖራል። ይህ ከመደበኛዉ የክፍል ዉስጥ ትምህርት በተጨማሪ የሚሰጥ ነዉ። በተግባር ልምምድ ወቅት ተሳታፊዎች ኖርዌይኛን በሥራ ቦታ ላይ እንዴት መናገር እንዳለባቸዉ ይማራሉ። ስለዚህ በተግባር የቋንቋ ልምምድ ሲያደርጉ ቋንቋዉን ከመማር በተጨማሪ በሥራ ቦታ ከሰዎች ጋር ይተዋወቃሉ።

ኖርዌይ ውስጥ ሥራ ማግኘት የሚፈልጉ ሰዎች ንቁና ቀልጣፋ መሆን አለባቸዉ። ቋንቋ መማር፣ ሌሎች ሰዎችን መተዋወቅና የሥራ ልምድ ማዳበር በጣም አስፈላጊ ነው። አንዳንድ ሰዎች በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ የሥራ ልምምድ ለማድረግ ዕድል ይሰጣቸዋል። የሥራ ላይ ልምምድ የሚያመቻቸው ናቭ ነዉ።

ከሌሎች ሃገሮች በተለያዩ ሙያዎች ሰልጥነው የመጡ ሰዎች ኖርዌይ ውስጥ ለሙያቸው የብቃት ማረጋገጫ እንዲሰጣቸው ማመልከት ይችላሉ። ማረጋገጫውን ለማግኘት የሚቻልባቸው በርካታ መንገዶች አሉ። ዝርዝር መረጃውን በ http://www.nokut.no/ ማግኘት ይቻላል።www.nokut.no.

አንድ ሰው በህብረተሰቡ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ መሆን የሚችለው በሥራው ዓለም በመሰማራት ብቻ አይደለም። በተለያዩ የበጐ ፈቃድ ማህበራት፣ በስፖርት ማህበራትና በፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ ድርጅቶች ውስጥ በመሳተፍ ከሰዎች ጋር መተዋወቅ፣ ቋንቋን መለማመድና የግል ችሎታንና ፍላጐትን መፈተሽና ማዳበርም ይቻላል።

ኖርዌይ ውስጥ ልጅ ያለዉ ሰዉ ከሌሎች ሰዎች ጋር ይበልጥ የመገናኘት ዕድል ይኖረዋል። የልጆች ህይወት በተለያዩ እንቅስቃሴዎች የተሞላ ነዉ። ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ወደ ትርፍ ጊዜ እንቅስቃሴዎች ሲሄዱ፥ ልጆችን ለሰውነት ማጎልመሻ ልምምድ ሲያደርሱ ወይም የወላጆች ስብሰባ ላይ ሲሳተፉ ከሌሎች ወላጆች ጋር ይተዋወቃሉ። ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀሱ ኖርዌያውያንም ይህን አጋጣሚ ከሰዎች ጋር ለመተዋወቅና ወዳጅነት ለመመሥረት ይጠቀሙበታል። ፍልሰተኞችም ተመሳሳይ አጋጣሚዎችን በመጠቀም ኖርዌይኛ ቋንቋቸውን ማዳበርና ሌሎች ሰዎችን መተዋወቅ ይችላሉ።

መረጃ

የቋንቋ መናገር የሚሰጠው

  • የቋንቋ ልምምድን
  • ዋጋ ያለው የስራ ልምድን
  • ጠቃሚ ዋቢዎችን
  • የሰው ትውውቅን

በኖርዌይ ልጅ አለዎት? ልጆች ከትምህርት ጊዜ በኋላ በተለያዩ እንቅስቃሴዎች ውስጥ እንዲሳተፉ ያድርጉ። ልጆችዎን ይከተሉ፣ በዚህም አጋጣሚ ከሌሎች ሰዎች የተዋወቃሉ።