ታሪክ፣ ህብረተሰብና የኑሮ ሁኔታ

ህብረተሰብ

Norge i Verden

የኖርዌይ አቀማመጥ በአለም

የኖርዌይ የቆዳ ስፋት 385,199 ካሬ ኪሎ ሜትር ነው። ይህም ሃገሪቱ ከታይላንድ፣ ኢራቅ፣ ቱርክ፣ ወይም ከሶማሊያ በመጠን ያነሰ የቆዳ ስፋት አላት ማለት ነው። የኖርዌይ ቅርፅ ወደ ጐን ጠበብ ያለ ሲሆን ከላይ ወደ ታች ደግሞ በጣም ረጅም ነው። ከኦስሎ እስከ ፓሪስ እና ከኦስሎ እስከ ትሮምስ ያለው ርቀት ተቀራራቢ ነው።

ኖርዌይ የምትገኘው ስካንዲኔቪያ ተብሎ በሚጠራውና ስዊድን፣ ዴንማርክ፣ ፊንላንድና አይስላንድን ጨምሮ በያዘው ክልል ውስጥ ነው። የኖርዌይ አጐራባች ሃገራት ስዊድን፣ ፊንላንድና ሩሲያ ናቸው።

ክልሎችር

ኖርዌይ በአምስት ክልሎች የተከፋፈለች ሲሆን እነርሱም፡- ሰሜናዊ ኖርዌይ፣ ትረንደላግ፣ ምዕራባዊ ኖርዌይ፣ ደቡባዊ ኖርዌይ እና ምሥራቃዊ ኖርዌይ ናቸው።

ዞኖች (ፍይልከዎች)

ኖርዌይ 11 ዞኖች (ፍይልከዎች) ያሉ ሲሆን እነዚህም በሃገሪቱ ክልሎች በሚከተለው መልኩ ተከፋፍለው ይገኛሉ:
ሰሜን ኖርዌይ: ኑርላንድን፣ ትሮምስ እና ፊንማርክ
ትረንደላግ: ትረንደላግ
ምዕራብ ኖርዌይ: ቬስትላንድ፣ ሩጋላንድ እና መረ እና ሩምስዳል
ደቡብ ኖርዌይ: አግደር
ምሥራቅ ኖርዌይ: ቬስትፎል፣ ቴሌማርክ፣ ቪከን፣ ኢንላንደ እና ኦስሎ

Norgeskart og flagg

ከተማዎች

ኖርዌይ ውስጥ አንድ መቶ የሚጠጉ ከተሞች አሉ። ኦስሎ ትልቋ ከተማ ስትሆን ወደ 6ዐዐ ዐዐዐ የሚጠጉ ህዝቦች ይኖሩባታል ። ከትልልቅ ከተሞች ውስጥ አስሩ በቅደም ተከተል (ከትልቁ ወደ ትንሹ) የሚከተሉት ናቸው።

   • ኦስሎ

Oslo

  • በርገን

Bergen Trondheim

 • ትሮንደሄይም
 • ስታቫንገር
 • ክርስቲያንሳንድ
 • ፍሬድሪክሰታድ
 • ትሮምሶ
 • ሳንድነስ
 • ድራመን
 • ሻሽቦረግ
 • ssb.no

 

ሌሎች መልክዓ ምድራዊ ጭብጦች

   • የኖርዌይ ትልቁ ተራራ ጋለደሆፒገን ይባላል። 2469 ሜትር ከፍታ አለው። ወደ ግማሽ የሚጠጋው የኖርዌይ ስፋት ተራራማ ነው።

  • የኖርዌይ ትልቁ ሀይቅ ምዮሳ ይባላል። ስፋቱም 365 ካሬ ኪሎ ሜትር ነው።
  • የኖርዌይ ትልቁ ወንዝ ግሎማ ይባላል። ርዝመቱም 611 ኪሎሜትር ነው።
  • በባህር ዳርቻም ብዙ የባህር ሸለቆ (ፍዮርድ) ያሉና ረጂሙም ሶግነፍዮርደን ይባላል። ይህም 204 ኪሎሜትር ርዝመትና 1308 ሜትር ጥልቀት አለው።

Sognefjorden

 • ግማሽ የሚጠጋው የኖርዌይ ምድር ተራራማ ሲሆን አንድ-ሦስተኛው ደግሞ በደን የተሸፈነ ነው። ከአጠቃላይ የኖርዌይ መሬት ያልለማው (ህንፃዎችና መንገዶች) ሁለት በመቶው ብቻ ነው።

መረጃ

መግቢያ

ኖርዌይ በአምስት መልክዓ ምድራዊ ክፍሎች የተከፋፈለች ስትሆን በአስተዳደራዊ ዘርፍ ደግሞ 11 ዞኖችና እና 356 የወረዳ (ኮምዩነ) መስተዳድሮች አሏት።

ተራራና ደን

በግምት ግማሽ የሚሆነው የኖርዌይ መሬት ተራራማ ነው። 38% የሚሆነው ደግሞ በደን የተሸፈነ ነው። የታረሰውን ደግሞ 3% ብቻ ነው።