ታሪክ፣ ህብረተሰብና የኑሮ ሁኔታ

አየር ሁኔታ

ኖርዌይ አራት ወቅቶች አሏት። እነርሱም ፀደይ (ቮር)፣ በጋ (ሶመር)፣ መከር (ኸስት) እና ክረምት (ቪንተር) ናቸው።.

የኖርዌይ የአየር ንብረት ክልል ወደ ክልል ይለያያል። በአንድ ክልል ውስጥ እንኳን የአየር ንብረት ልዩነት የሚስተዋል ሲሆን ከዓመት ዓመት ከፍተኛ ተለዋዋጭነት ሊታይ ይችላል። በአጠቃላይ ግን ጠረፋማ አካባቢዎች ዝቅተኛ በረዶ የሚጥልበት መካከለኛ የክረምት ጊዜ ሲኖራቸው፣ በመሃል አገር የሚገኙት ደግሞ ብዙ በረዶ የሚጥልበት ቀዝቃዛ ክረምት አላቸው። በሌላ በኩል ወደ መሃል ሃገር የበጋው ወቅት ሞቃትና ደረቅ ነው። ምዕራባዊው ኖርዌይ ከምሥራቃዊው ኖርዌይ የተሻለ ዝናብ ያገኛል።
በባህር ዳርቻ ያሉት አካባቢዎች በተለይ በመከር (ኸስት) ወቅት ነፋሻማ ናቸው።

ሰሜናዊና ደቡባዊ የሃገሪቱ ክፍሎች የሚያገኙት የቀን ብርሃን መጠን በጣም ይለያያል። በክረምት ወቅት ወደ ሰሜን ከፍ እያልን ስንሄድ የቀን ጊዜ እያጠረ ይሄዳል። በአውሮፓ የሰሜን ጫፍ የብስ ላይ የምትገኝ ከተማ በምትባለው ሐመርፌስት በክረምት ወቅት ረጅሙ የጨለማ ጊዜ ለሁለት ወራት ይዘልቃል። በዚህ ወቅት ምንም የቀን ብርሃን የለም። በተቃራኒው ደግሞ በበጋ ወቅት ለሁለት ወራት ያህል ጨለማ የሚባል የለም። በዚህ ወቅት እኩለ ሌሊት ላይም ፀሐይ ትወጣለች።

Midnattssol

በደቡባዊ የሃገሪቱ ክፍሎችም በበጋና በክረምት ወቅቶች ከፍተኛ የሆነ የቀን ርዝመት ልዩነቶች አሉ። ይሁን እንጂ ደቡባዊ አካባቢዎች በእኩለ ሌሊት የምትወጣዉን ፀሐይም ይሁን ረጅም የጨለማ ወቅት አያዩም።

የጨለማ ጊዜና የእኩለ ሌሊት ፀሐይ ያላቸው አካባቢዎች መለያው ከሙ ኢ ራና ወደ ሰሜን ትንሽ ከፍ ብሎ የሚገኘው የዋልታ ክበብ ነው።

መረጃ

የአየር ሁኔታ

በኖርዌይ ታሪክ የተመዘገበው በጣም ከፍተኛው የሙቀት መጠን 35.6 ዲግሪ ሴልሸስ ሲሆን፣ ይኸውም በኔስብየን በጁን 20፣ 1970 ነው።

በኖርዌይ እስካሁን የተለካው ከፍተኛው ቅዝቃዜ – 51.4 ድ.ሴ. ነው (በካራሾክ ጃኗሪ 1 ቀን 1886)

መካከለኛ የውቅያኖስ ንፋስ

ምንም እንኳ ኖርዌይ በዓለም በሰሜን ጫፍ ከሚገኙት የበለጠ ሰሜን ብትሆንም ከአብዛኞቹ አየር ፀባዩ መካከለኛ ነው። ይህም የሆነበት ምክንያት በመካከለኛው አሜሪካ የሚገኘው የባህረ ሰላጤ እስከ ኖርዌይ የባህር ዳርቻ የሚመጣው የውቅያኖስ ንፋስ ስለምያሞቀው ነው።