ታሪክ፣ ህብረተሰብና የኑሮ ሁኔታ

ሃይማኖቶችና እምነቶች

Religiøse symboler

ኖርዌይ ውስጥ የሃይማኖት ነፃነት ሙሉ በሙሉ ይከበራል። ይህ ማለት ማንኛውም ሰው ያለምንም ሥጋትና የመሳደድ ፍርሃት የመረጠውን ሃይማኖት መከተል ይችላል። እያንዳንዱ ሰው የፈለገውን ሃይማኖት በነፃነት መምረጥና መከተል ይችላል። በተመሳሳይ ማንኛውም ሰው የትኛውንም ሃይማኖት ያለመከተል ነፃነት አለው።

የኖርዌይ ቤተክርስቲያን ብሔራዊ ቤተ-ክርስቲያን ስትሆን በሃገሪቱ ከሚገኙ የሃይማኖት ተቋማት በጣም ትልቋ ናት። ይህም ማለት በመርህ ደረጃ ክርስትና መነሳትን የተመረኮዘ ሲሆን የቤተክርስትያኗ አባልነታቸውን ያልሰረዙ ሰዎችን በሙሉ ያጠቃልላል። በመሆኑም 75 በመቶ የሚጠጋው የሃገሪቱ ህዝብ የቤተ-ክርስቲያኗ አባል ነው። ምንም እንኳን የቤተክርስቲያን አባላት ቁጥር ከፍተኛ ቢሆንም ሃይማኖት በእያንዳንዱ ሰው የዕለት ተዕለት ህይወት ውስጥ ጉልህ ሚና አለው ማለት አይደለም። ለምሳሌ የስታቲስቲክስ መረጃዎች እንደሚያሳዩት በወር ከአንድ ጊዜ በላይ ቤተክርስቲያን የሚሄዱት ኖርዌያውያን አስራሁለት በመቶዎቹ ብቻ ናቸው። ሰላሳ ሰባት በመቶዎቹ ደግሞ በጭራሽ ቤተ-ክርስቲያን እንደማይሄዱ ይገልፃሉ። ይሁን እንጂ ለክርስትና ለመነሳት፣ እምነት መቀበልን ለማረጋገጥ፣ ለሰርግ፣ ለሥርዓተ ቀብር እና ለገና ክብረ በዓላት ቤተ-ክርስቲያኗ አሁንም ለብዙ ዜጐች አስፈላጊ ናት።

የተለያዩ የእምነት ተቋማት ከመንግሥት የገንዘብ ድጋፍ ይደረግላቸዋል።

የእምነትና የርእዮተ አለም ተቋማት ከመንግሥትና ከወረዳ (ኮሚዩነ) የገንዘብ ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ። ዕውቅና ያላቸው የሃይማኖት ተቋማት ለእያንዳንዱ አባሎቻቸው ከመንግሥት የሚያገኙት ድጋፍ የኖርዌይ ቤተክርስቲያን አባላት ከሚያገኙት ድጋፍ ጋር አንድ ዓይነት ነው።

ኖርዌይ ብዝሃ-ባህልና አለማዊ ህብረተሰብ ያላት ሃገር ናት።

Moské Ei kyrkje Shiva

ኖርዌይ ክርስትናን የተቀበለች ከ1ዐዐዐ ዓመታት በፊት ሲሆን፣ በ15ዐዐዎቹ ከተካሄደው የሃይማኖት ተሃድሶ ወዲህ የሉተራን ክርስትና (ፕሮቴስታንት እምነት) በሃገሪቱ ከፍተኛ ተከታዮች ያለው ሃይማኖት ነው።

ድሮ ኖርዌያውያን ከብሔራዊ ቤተክርስቲያኗ መውጣት አይፈቀድላቸውም ነበር። ከክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ያልሆኑ በራሳቸው እምነት መደራጀት በህግ የተፈቀደላቸው ከ185ዐ ወዲህ ነው።

አሁን ያለው የኖርዌይ ህብረተሰብ መካከል አለማዊነት በጣም እየተስፋፋ ይገኛል። ስለሆነም በግለሰቦች ህይወትም ሆነ ብሔራዊ ህጐች በሚቀረፁበት ጊዜ ሃይማኖት በህብረተሰቡ ውስጥ ያለው ሥፍራ ከድሮው በእጅጉ ቀንሷል።

የተለያዩ የሃይማኖትና የህይወት ርእዮተ አለም ቡድኖች በኖርዌይ

ከኖርዌይ አጠቃላይ ህዝብ 25 በመቶ የሚጠጋው የብሔራዊ ቤተ-ክርስቲያን አባል አይደለም። ከእነዚህ ውስጥ ግማሽ ያህሉ የሌላ ሃይማኖት ወይም የህይወት ርእዮተ አለም ተቋም ተከታይ ሲሆን ቀሪው ግማሽ ደግሞ የምንም ዓይነት ተቋም አባል አይደለም።

ከኖርዌይ ብሔራዊ ቤተ-ክርስቲያን ውጭ ያሉ ሃይማኖቶችን እና የህይወት ርእዮተ አለም የሚከተሉ ማህበረሰቦች ስርጭት የሚከተለው ነው።

Medlemmer i tros- og livssynssamfunn utenfor Den norske kirke

መረጃ

የህዝብ ቤተ ክርስቲያን

  • የኖርዊጂያን ቤተ ክርስቲያን የህዝብ ቤተ ክርስቲያን ነው። ይህም በኖርዌይ ትልቁ ሀይማኖት ሲሆን የሉተራንና የፕሮተስታንት ክርስትና እምነትን ያራምዳል።
  • የኖርዊጂያን ቤተ ክርስቲያን ቀደም ሲል የመንግስት ቤተ ክርስቲያን ነበር።
  • ከሜይ 21 ቀን 2012 ጀምሮ ኖርዌይ የመንግስት ቤተ ክርስቲያን የላትም።