ታሪክ፣ ህብረተሰብና የኑሮ ሁኔታ

ሰፈራና ህዝብ በኖርዌይ

  • ኖርዌይ ውስጥ ከአምስት ሚሊዮን በላይ ህዝብ ይኖራል።
  • ከዚህ ውስጥ 75 በመቶ የሚሆነው ህዝብ በባህር ዳርቻ ይኖራል።
  • ግማሽ የሚደርሰው የኖርዌይ ህዝብ የሚኖረው በምሥራቃዊ ኖርዌይ ነው።
  • ከአጠቃላዩ የኖርዌይ ህዝብ 17 በመቶ የሚጠጋው ፍልሰተኛ ወይም የኖርዌይ ተወላጅ የፍልሰተኛ ልጅ ነው። አብዛኞው ፍልሰተኛ ወይም የኖርዌይ ተወላጅ የፍልሰተኛ ልጅ የሚኖርባቸው ከተሞች ኦስሎና ድራመን ናቸው።
  • ስለኖርዌይ ህዝብ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት የሚከተለውን ድረ-ገፅ መመልከት ይቻላል፡-
    www.ssb.no

መረጃ

የሳም ህዝብ

በኖርዌይ ውስጥ የሚኖሩ ሳም የሚባሉ አናሳ ብሔረሰቦች አሉ፣ እነዚህ ሳም ህዝቦች በኖርዌይ ረጅም ጊዜ የሩ ህዝቦች ናቸው። ከ 40000 እስከ 50000 የሳም ህዝቦች በኖርዌይ ይኖራሉ። በስዊድን፣ በፍንላንድና ሩሲያ በአንድ ላይ ወደ 50000 የሚሆኑ የሳም ህዝቦች ይኖራሉ። የሳም ህዝብ የራሱ ሳምስክ የሚባል ቋንቋ አለው። የተለያዩ የሳም ቋንቋዎች አሉ።
ሳሞች ከ 1989 ዓ.ም ጀምሮ የራሳቸው የሆነ ፓርላማ አላቸው። በሳም ፓርላማ የሳም ህዝብን የሚመለከት ጉዳይ ይመከራል። ነገር ግን የኖርዊጂያን ህገ መንግስት እንደማንኛውም በኖርዌይ የሚኖር ሁሉ የሳም ህዝብንም ይመለከታል።