ዲሞክራሲና የማህበራዊ ዋስትና ሥርዓት

ምርጫና የፖለቲካ ፓረቲዎች

ምርጫ

ኖርዌይ ውስጥ እያንዳንዱ በየአራት ዓመት የሚካሄድ ሁለት ዓይነት የፖለቲካ ምርጫ ይካሄዳል። እነዚህም የዞንና የወረዳ ምርጫ እና የተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ ናቸው። ሁለቱ ምርጫዎች በተመሳሳይ ጊዜ ሳይሆን በየተራ በሁለት ዓመት ልዩነት ይካሄዳሉ።

I avlukket En dame som stemmer ved valg

የፖለቲካ ፓርቲዎች በሚያካሂዱት ስብሰባ የፓርቲያቸውን ዕቅዶች (መርሀ ግብሮች) ይቀርፃሉ። በቀጣዮቹ አራት ዓመታት ማለትም በሚቀጥለው የምርጫ ጊዜ የሚያተኩሩባቸውን ርዕሰ ጉዳዮች በዝርዝር ይለያሉ።

ኖርዌይ ውስጥ ምርጫ የሚካሄደው በሚስጥር በሚሰጥ ድምፅ ነው። በመሆኑም አንድ ሰው ድምፁን ለማን እንደሰጠ ማንም ማወቅ አይችልም። ድምፅዎን ለፈለጉት ፓርቲ መስጠት ይችላሉ። የአንድ ቤተሰብ አባላት ለተለያዩ ፓርቲዎች ድምፅ መስጠት ያልተለመደ ክስተት አይደለም።

የፖለቲካ ፓርቲዎች

ኖርዌይ ውስጥ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስለሚገኙ በምርጫ ወቅት በርካታ አማራጮች ይኖራሉ። ኖርዌይ ውስጥ 2ዐ የሚደርሱ የተለያዩ ፓርቲዎች ይገኛሉ።

የኖርዌይ ትልቅ የሚባሉት ፖለቲካ ፓርቲዎች ከግራ ክንፍ «ሶስያሊስቲስክ» እስከ ቀኝ ክንፍ «ቦርገርሊ» ድረስ በደረጃ ስናስቀምጣቸው፡- Rødt SV Ap SP KrF Venstre Høyre FrP

መደበኛ እና ኢመደበኛ ስልጣን

የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ህግጋት፣ የህግ ለውጦች እና በጀት ያጸድቃሉ። በዚህ መልኩም በወረዳ እና በሃገራዊ ደረጃ የሚተገበረው የፖለቲካ አይነት የመወሰን መደበኛ ስልጣን አላቸው። በተጨማሪም ኢመደበኛ ብለን የምንጠራው ስልጣን ያላቸው ብዙ አካላቶች አሉ። ይህ ማለት ፖለቲካው ላይ በተለያየ መልኩ ተጽእኖ ያሳድራሉ ማለት ነው።

መገናኛ ብዙሃን
የኖርዌይ መገናኛ ብዙሃን (ሬድዮ፣ ቴሌቪዥን፣ ኢንተርኔት፣ ጋዜጦች ወዘተ.) ነጻ ናቸው። ይህ ማለት ስልጣን ላይ ያለው የፖለቲካ ፓርቲ ሳይበግራቸው የፈለጉትን መረጃ ማተም ይችላሉ። ያም ሆኖ ግን መገናኛ ብዙሃኑ ጭምር ሃሳብን በነጻ የመግለጽ መብት የሚያስቀምጠውን ገደብ መተላለፍ አይችሉም። መገናኛ ብዙሃን ትልቅ ትጽእኖ የመፍጠር ሃይል አላቸው። መገናኛ ብዙሃን አነጋጋሪ አርእስቶችን የመወሰን፥ ስህተት ወይም ጉድለት የመጠቆምና የመቆጣጣር ሚና ይጫወታሉ ይባላል። በዚህ መልኩ ተራ ተመልካቾች፣ አንባቢዎች ወይም አድማጮች እና እንዲሁም ፖለቲከኞች ላይ ተጽእኖ ያሳድራሉ።

ማህበራት
ኖርዌይ ውስጥ የመደራጀት ነፃነት አለ።
ይህ ማለት ነዋሪዎች የተለያዩ ማህበራት የመመስረትም ሆነ በአባልነት የመቀላቀል ነጻነት አላቸው።

የማህበራት ዓይነቶች ለምሳሌ ያህል

  • የአካል ጉዳተኖች እና ሕመምተኞች ማህበራት
  • የሴቶች መብት ማህበራት
  • የልጆች መብት ማህበራት
  • የአካባቢና የተፈጥሮ ጥበቃ ማህበራት
  • በየወራዳው ለተለያዩ ጉዳዮች የሚታገሉ ማህበራት

እንደ መገናኛ ብዙሃኑ እነዚህ ማህበራትም ትልቅ ተጽእኖ የማሳደር ሃይል አላቸው።
ተራ ተመልካቾች፣ አንባቢዎች ወይም አድማጮች እና እንዲሁም ፖለቲከኞች ላይ ተጽእኖ ያሳድራሉ።
ሰዎች ወይም ድርጅቶ/ማህበራት ኢመደበኛ በሆነ መልኩ ፖለቲከኞች እና ውሳኔዎቻቸው ላይ ተጽእኖ ለማሳደር ሲሞክሩ የማግባባት ስራ ወይም ሎቢይዝም ብለን እንጠራዋለን።

መረጃ

የመምረጥ መብት

  • በኖርዌይ የመምረጥ መብት እድሜ 18 ነው።በፓርላማ ምርጫ ለመሳተፍ የኖርዊጂያን ዜጋ መሆን አለብዎት።
  • በዞንና በወረዳ ምርጫ ድምፅ ለመስጠት ከምርጫው በፊት ሶስት ዓመት በኖርዌይ መኖር ይኖርብዎታል።
  • በ1913 ዓ. ም ሴቶች የመምረጥ መብት ካገኙበት ጊዜ አንስቶ በኖርዌይ ሁሉም የመምረጥ መብት አለው።