ዲሞክራሲና የማህበራዊ ዋስትና ሥርዓት

የኖርዌይ ንጉሰ ነገስት

Kongeparet og Kronprinsparet, (Foto: Sølve Sundsbø / Det kongelige hoff)

ኖርዌይ ንጉሣዊ ሥርዓት ያላት ሃገር ናት። በንጉሣዊ ሥርዓት ውስጥ የሃገሪቱ ርዕሰ ብሔር ንጉሥ ወይም ንግሥት ናቸዉ። ኖርዌይ ውስጥ የንጉሡ የፖለቲካ ሥልጣን በጣም አነስተኛ ቢሆንም ንጉሡ በየሳምንቱ የካቢኔ ስብሰባ የሚያካሂዱት መደበኛ የሥራ ድርሻ አላቸው። በተጨማሪም በመንግሥት ኦፊሴላዊ ውሳኔዎች ላይ ፊርማቸውን ያኖራሉ እንዲሁም ምክር ቤቱ የሚያፀድቃቸውን ህጐች ያፀናሉ።

ንጉሡ ወይም ንግሥቷ የሚመረጡት በፖለቲካ ምርጫ በሚደረግ ህዝበ ውሳኔ አይደለም። የንግሥና ሥልጣን ከወላጅ ወደ ልጅ በውርስ የሚተላለፍ ነው።የአሁኑ የኖርዌይ ንጉሥ ሃራልድ 5ተኛ ናቸው። ባለቤታቸው ንግሥት ሶንያ ናቸው። የንጉሡና ንገሥቷ ሁለት ልጆች ልዕልት ማርታ ሉዊስ (በ1971 የተወለዱ) እና ልዑል አልጋ ወራሽ ሃኮን ማግኑስ (በ1973 የተወለዱ) ናቸው። ልዑል አልጋወራሽ ሃኮን ማግኑስ የንግሥና ሥልጣንን ከአባታቸው ይወርሳሉ። የእርሳቸው ልጅ ልዕልት ኢንግሪድ አሌክሳንድራ (በ2ዐዐ4 የተወለዱ) ከልዑሉ ቀጥለው ይነግሳሉ ማለት ነው።

Kong Harald, Kronprins Haakon og Prinsesse Ingrid Alexandra, (Foto: Morten Brun, Det kongelige hoff)

መረጃ

ነገስታት

ከስዊድን ጋር የነበረው ህብረት በ1905 ዓ.ም ከፈረሰ ወዲህ ኖርዌይ ሶስት ንጉሶች አንግሳለች።

    • ሃኩን 7ኛ (1905- 1957 ንጉስ)
    • ኡላቭ 5ኛ (ከ1957- 1991 ንጉስ)
    • ሃራልድ 5ኛ (ከ1991 – እስከ ዛሬ ንጉስ)

Kong Haakon med kronprins Olav på armen, 1905, (Oslo Museum, ukjent fotograf)