ዲሞክራሲና የማህበራዊ ዋስትና ሥርዓት

የድጋፍ ዋስትና ማህበረሰብ

ማህበራዊ ዋስትና ሥርዓት ማለት የነዋሪዎች መሠረታዊ የኑሮ ደረጃ እንዲሁም ትምህርትና የጤና እንክብካቤ ከግብር በሚገኝ ገቢ የሚደገፍበት ሥርዓት ማለት ነው። የመንግሥት ጥቅማ ጥቅሞች የሁሉም ነዋሪዎች ሃብት ናቸው። ስለዚህ ማህበራዊ ዋስትና ሥርዓት መሠረታዊ የሆኑ ፍላጐቶቹን ለምሳሌ መኖሪያ ቤት፣ ምግብ፣ የህክምና አገልግሎትና ትምህርት እንዲሟላ ይደረጋል።

ኖርዌይ የማህበራዊ ዋስትና ሃገር ትባላለች። ምክንያቱም የማህበራዊ ዋስትናው ዋነኛው ኃላፊነት የመንግሥት እና ወረዳዎ ስለሆነ ነው።

የማህበራዊ ዋስትና ድጋፍ በዋናነት ገንዘብ የሚያገኘው ከዜጐች በሚሰበሰብ ቀረጥና ግብር ነው። በተጨማሪም መንግሥት ከነዳጅ ዘይትና ጋዝ ሽያጭ ከሚያገኘው ገቢ ለማህበራዊ ዋስትና ድጋፍ ያደርጋል።

ለማህበራዊ ዋስትና ድጋፍ ዋነኛው ኃላፊነት የመንግሥት ቢሆንም መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና የግል ድርጅቶችም ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋሉ።

መረጃ

የመደጋገፍ ህብረተሰብ ሥርዓት

  • የመደጋገፍ ህብረተሰብ ሥርዓት ከፍተኛና የተመጣጠነ የድጋፍ ማከፋፈል ህብረተሰብ ሥርዓት ነዉ። መደጋገፍ ስርዓቱ ገንዝብ ያስወጣል።
  • በኖርዌይ የሚኖሩት ሁሉ የድጋፍ ስር ዓቱን በቀረጥና ወጪዎች በመክፍል ይሳተፋል።