ዲሞክራሲና የማህበራዊ ዋስትና ሥርዓት

የድጋፍ ዋስትና ማህበረሰብ ዋና ዋና ስራዎች

በኖርዌይ የማህበራዊ ዋስትና ሥርዓት የመንግሥት ኃላፊነት ከፍተኛ ነው። መንግሥት፣ ዞኖች እና ወረዳዎች ከፍተኛውን ገንዘብ ድጋፍ ከማድረጋቸውም በላይ ዜጐች የዋስትና ሥርዓቱን ደንቦች በትክክል ማክበራቸውን ይከታተላሉ። ዓላማው ሁሉም ዜጐች እኩል እንዲስተናገዱና ፍትሃዊ የጥቅማ ጥቅሞች ክፍፍል እንዲኖር ነው።

በብዙ ህብረተሰቦች ውስጥ የቤተሰብ አባላት ችግር ሲገጥማቸው እርዳታ የመስጠት ኃላፊነት የሚወድቀው በቤተሰቦች ላይ ነው። ኖርዌይ ውስጥም የቤተሰቦችና የጓደኞች መረዳዳት የተለመደ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት አብዛኛውን ኃላፊነት መንግሥት ወስዷል።

የማህበራዊ ዋስትና ሥርዓት ለዜጐቹ በርካታ ማህበራዊ ጥቅሞች ይሰጣል። ሆኖም ዜጐችም የራሳቸው ኃላፊነት እንዳለባቸው መዘንጋት የለበትም። የማህበራዊ ዋስትና አገልግሎት በአግባቡ መሥራት እንዲችል በጣም አስፈላጊው ቅድመ ሁኔታ መተማመን ነው። አንድ ሰው ላይ እምነት ሲኖረን በእርሱ ላይ ያለን መተማመን ይጨምራል።

አገልግሎቱ ሲያስፈልገን በማህበራዊ ዋስትና ሥርዓት ውስጥ ባለው አሰራር ላይ እምነት ሊኖረን ይገባል። በሌላ በኩል መንግሥት እና ወረዳዎችም ዜጐች ትክክለኛ መረጃ እንደሚሰጡና አገልግሎቱን ያለአግባብ እየተጠቀሙት እንዳልሆነ እምነት ሊያድርባቸው ይገባል።

መረጃ

የመደጋገፍ ሥርዓት ዓላማው ለሁሉም ዋስትና መስጠትና የድጋፍ እሴቶችን ሳያዳሉ ማከፋፈል ነው።

የመደጋገፍ ሥርዓቱ የተመሰረተው በመተማመን ላይ ነው።

የመደጋገፍ አስተዳደር የሚከተሉት ሃላፊነቶች አሉት፣

  • የነዋሪዎች ጤና
  • የነዋሪዎች ትምህርት
  • የልጆች እንክብካቤ
  • የአረጋውያንና ድጋፍ ለሚፈልጉት እንክብካቤ
  • ለእንዳንዱ ነዋሪ የኢኮኖሚ ዋስትና