ዲሞክራሲና የማህበራዊ ዋስትና ሥርዓት

የዋስትና ጥቅማጥቅም

En eldre dame får medisinsk hjelp Personer i rullestol Eldre par Elever på biblioteket Barnehage Nyfødt barn på vekt
እነዚህ ምስሎች ለኖርዌይ ህብረተሰብ ከሚሰጡ የማህበራዊ ዋስትና ጥቅሞች ጥቂቶቹን ያሳያሉ።

የማህበራዊ ዋስትና ጥቅሞች ሁሉን አቀፍ ናቸው።ይህ ማለት ሁሉም ሰው ጥቅሞቹን የማግኘት መብት አለው ማለት ነው።

ምንም እንኳን ማንኛውም ሰው የማህበራዊ ዋስትና አገልግሎቶችንና ጥቅሞችን የማግኘት መብት ቢኖረውም ሁሉንም ዓይነት ጥቅሞች የግድ ያገኛል ማለት አይደለም።

አንዳንድ የማህበራዊ ዋስትና አገልግሎቶችን አብዛኛዎቻችን ለረጅም ጊዜ እንጠቀምባቸዋለን። ለምሳሌ ሁሉም ልጆችና ወጣቶች ለአስር ዓመታት ትምሀርት የመከታተል የውዴታ ግዴታ አለባቸው። ተማሪዎች ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መቀጠልም ይችላሉ። አብዛኛዎቻችንም ረጅም ዕድሜ የመኖርና ጡረተኞች የመሆን ዕድል ይኖረናል።

አንዳንድ ማህበራዊ አገልግሎቶችን ደግሞ በህይወታችን አንዴ ብቻ ወይም ከዚያ በላይ ልንጠቀም እንችላለን። ኖርዌይ ውስጥ ሆስፒታል ተኝቶ የመታከም አገልግሎት የሚሰጠው በነፃ ሲሆን፣ ሐኪም ሲመረምረን ግን የተጠቃሚ የክፍያ ድርሻ እንከፍላለን።

ሌሎች የማህበራዊ ዋስትና አገልግሎቶች በህይወታችን ከፍተኛ ችግሮች ሲያጋጥሙን የሚያግዙን ናቸው። ለምሳሌ የሥራ አጥነት አበልና በህመም ምክንያት ሥራ መሥራት ሳንችል ስንቀር የምናገኛቸው ጥቅሞች ይጠቀሳሉ። በእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ ስንሆን የሚሰጠን የገንዘብ ድጋፍ ጊዜያዊ ሲሆን ዓላማውም ሁኔታዎች እስኪስተካከሉልን ድረስ ለማገዝ ነው።

መረጃ

ለማህበረሰቡ የሚሰጠው የተለያዩ አገልግሎቶች የመደጋገፍ እሴቶች እንላቸዋለን።

  • አንዳንድ የመደጋገፍ እሴቶችን በህይወት ለረጅም ጊዜ እንጠቀምባቸዋለን።
  • አንዳንድ የድጋፍ እሴቶችን አንዳንዴ ብቻ እንጠቀምባቸዋለን።
  • አንዳንድ የድጋፍ እሴቶችን ምናልባት አንጠቀምበትም።