ዲሞክራሲና የማህበራዊ ዋስትና ሥርዓት

የስራና የድጋፍ ዋስትና ቢሮ

ኖርዌይ ውስጥ የሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች የሠራተኛና ማህበራዊ ዋስትና አገልግሎት ጽ/ቤት አላቸው። ሥራ ለማግኘት ብቁ የሚያደርገንን ሥልጠና ሲያስፈልገን፣ ወይም ህመም ሲያጋጥመንና በተለያዩ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ስንሆን የገንዘብ ድጋፍ የምናገኘው ከዚህ ጽ/ቤት ነው።

በተጨማሪ የኖርዌይ ሠራተኛና ማህበራዊ ዋስትና አገልግሎት (ናቭ) ለሃገሪቱ የማህበራዊ ደህንነት አስተዳደር ኃላፊነት አለበት። ማህበራዊ ድጋፍ የመስጠት ኃላፊነትም አለበት። ምንም እንኳን ከዓላማዎቹ ዉስጥ አንዱ ብዙ ሰዎች የሥራ ኃይሉን እንዲቀላቀሉ ማገዝ ቢሆንም ናቭ ሁላችንም ሥራ የማስያዝ ኃላፊነት የለበትም።

መረጃ

ከስራና የድጋፍ ቢሮ ዓላማዎች ጥቂቶቹ

    • ብዙዎች ወደ ስራ እንዲሰማሩና የሚረዱት አነስተኛ እንዲሆኑ ማድረግ
    • ጥሩ የስራ ገበያ እንዲኖር ማመቻቸት
    • የተጠቃሚዎችን ፍላጎትና መስፈርት ያሟላ አገልግሎት መስጠት

NAV