ዲሞክራሲና የማህበራዊ ዋስትና ሥርዓት

የድጋፍ ዋስትና ማህበረሰብ መብቶችና ግዴታዎች

የማህበራዊ ዋስትና አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ የተመሰረተው የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ የሚችሉ ሰዎች በሚሰጡት ድጋፍ ነው። የምንከፍለው ግብር ገቢነቱ ለህብረቱ ነው ። በህይወት ዘመናችን የተለያዩ የማህበራዊ ዋስትና ድጋፎችን እንጠቀማለን። ማንኛውም ሰው በህይወቱ ውስጥ የማህበራዊ ዋስትና ድጋፍ የሚፈልግበት ሁኔታ ሊያጋጥመው ይችላል። ድንገተኛ አደጋ ወይም ከባድ ህመም እንዲሁም ሥራ ማጣት ወይም ሌሎች ቀውሶች በየትኛውም ጊዜ ሊያጋጥሙ ይችላሉ። በእንደዚህ ዓይነት ጊዜያት የሚረዳን አካል መኖሩን ማወቅ መልካም ነገር ነው።

አንድ ሰው ጤናማ ሲሆንና ሥራ መሥራት ሲችል ግብር በመክፈል አስተዋፅኦ ያደርጋል። በመሆኑም ከዚህ በፊት ለተደረገልን ወይም ወደፊት ለሚያስፈልገን አገልግሎት መልሰን እንከፍላለን ማለት ነው። ስለዚህ ብዙ ሰዎች ይህ ሥርዓት ጥሩ እንደሆነ ያምናሉ። በማህበራዊ ዋስትና ሥርዓት ህዝቡ ገንዘብ ነክ መብቶችና ግዴታዎች አሉት።

  • ከመብቶች ውስጥ የህመም ክፍያ፣ የሥራ አጥነት አበል፣ የመሰናድዖ መርሀ ግብር አበል፣ የልጅ አበልና የጡረታ አበል የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ።
  • ከግዴታዎች ውስጥ ለምሳሌ ግብር መክፈል፣ የገንዘብ ድጋፍ አልግሎትን ያለአግባብ አለመጠቀምና ስለኑሮ ሁኔታ ትክክለኛውን መረጃ ለመንግስት መስጠት ይጠቀሳሉ።

መረጃ

ነፃነትና ሃላፊነት

  • በኖርዌይ በመደጋገፍ ላይ በተመሰረተ ሥርዓት የሚኖር ሁሉ ነፃነትና ሃላፊነት፣ መብትና ግዴታ አለው።
  • ኑሮአችንን እንዴት እንደምንኖር ለመምረጥ ነፃነት አለን። በተመሳሳይ ሁኔታ ሥርዓቱ እንደታሰበው እንዲያገለግል ሃላፊነትና ህግና ደንብን መከተል አለብን።