ዲሞክራሲና የማህበራዊ ዋስትና ሥርዓት

ታሪካዊ እድገት

ለድሆች ከሚደረግ ዕርዳታ ወደ ማህበራዊ ዋስትና ድጋፍ

Suppeservering for vanføre, 1905, (Oslo Museum, fotograf: Anders Beer Wilse)

ከታሪክ አኳያ አሁን ኖርዌይ ውስጥ ያለው የማህበራዊ ዋስትና ሥርዓት ረጅም ዕድሜ ያስቆጠረ አይደለም።አሁን ያለው የኖርዌይ ማህበራዊ ዋስትና ሥርዓት ለሁሉም ነዋሪዎች ነው። ከ100 ዓመታት በፊት ግን ሁኔታው ከአሁኑ የተለየ ነበር። በዚያን ጊዜ በነበረው ስርዓት የማህበራዊ እርዳታ ሰጪ ስርዓት ይባል ነበር። የመንግሥትን ድጋፍ የሚያገኙት እጅግ ደካማና እጅግ ደሃ የሆኑ የህብረተሰቡ አባላት ብቻ ነበሩ። የሚሰጠው የዕርዳታ ዓይነትም ከቦታ ቦታ በጣም ይለያይ ነበር።

አብዛኛዎቹ የማህበራዊ ዋስትና ጥቅማጥቅሞች ተግባራዊ መደረግ የጀመሩት ቀስ በቀስ ነው። አንዳንዶቹ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት (1940 – 1945) ጥቂት ቀደም ብለው የተጀመሩ ሲሆን፣ አብዛኛዎቹ ግን ከጦርነቱ በኋላ ከትግል በኋላ ህጋዊነት አግኝተዉ ተግባራዊ የሆኑ ናቸው።

ይሁን እንጂ ኖርዌይ ውስጥ አንድ የማህበራዊ አገልግሎት በጣም ረጅም ዘመን አስቆጥሯል፤ ይህም ከ1739 ጀምሮ ሲሆን ነፃ ትምህርት ለልጆች! የሚለው ነው።

አብዛኛዎቹ የማህበራዊ ዋስትና ጥቅማ ጥቅሞች የተጀመሩት ሠራተኞች ስለታገሉላቸው ነው። ባለፉት ከ60 እስከ 70 ዓመታት ባሉት ውስጥ መንግሥት የዜጐቹን ማህበራዊ ዋስትና የማረጋገጥ ኃላፊነት እንዳለበት ሰፊ የሚባል የፖለቲካ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

Slumsøster hos den syke, 1908 Arbeidsstue for barn, ca 1920 Frelsesarmeens suppekjøkken for uteliggere, 1920 Kø ved Christiania Dampkjøkken, 1903 Arbeidsstue for barn (1920)

መረጃ

ታሪክ እድገት

  • 1909፣ የታማሚ ዋስትና ህግ
  • 1915፣ የሥራ ሰዓት ህግ(ቢበዛ በቀን 10 ሰዓትና በሳምንት 54 ሰዓት)
  • 1935፣ የሥራ አጥነት ዋስትና ህግ
  • 1937፣ የሰራተኛ መብት ህግ (በክፍያ 9 ቀናት እረፍት)
  • 1946፣ የልጆች ድጋፍ ክፍያ ስራ ላይ ዋለ
  • 1956፣ የታማሚ ዋስትና ክፍያ ለሁሉም
  • 1957፣ የስራ ላይ ጉዳትና የእድሜ ዋስትና
  • 1960፣ መስራት ላልቻለ ዋስትና ክፍያ
  • 1965፣ ባለቤት የሞተበትና የእናት ዋስትና ክፍያ
  • 1967፣ የህዝብ ድጋፍ ዋስትና ህግ