ልጅና ቤተሰብ

ቤተሰቦች

Foreldre og barn

ኖርዌይ ውስጥ በየዓመቱ 6ዐ ዐዐዐ የሚደርሱ ህፃናት ይወለዳሉ።
ኖርዌይ ውስጥ የሚኖሩ ሴቶች እያንዳንዳቸው በአማካይ 1.5 ልጆች ይኖራቸዋል።
ሶስት አራተኛ የሚሆኑ ልጆች ከእናትና ከአባታቸው ጋር አብረው ይኖራሉ። አንድ አራተኛ የሚሆኑት ልጆች ደግሞ ከአንድ ወላጅ ጋር ብቻ ወይም ደግሞ ከአንደኛው ወላጅ እና ከወላጁ አዲስ የፍቅር አጋር ጋር ይኖራሉ።

Eit ungt par Mor, far og to barn Eit homofilt par Eit eldre par Far og dotter

አብረው ከሚኖሩ አራት ጥንዶች ውስጥ ሦስቶቹ ጋብቻ የፈፀሙ ሲሆን፣ ቀሪዎቹ ግን ሳይጋቡ አብረው ይኖራሉ። ለመጀመሪያ ጊዜ ትዳር ለመመሥረት አማካዩ ዕድሜ ለወንድም ሆነ ለሴት ከሰላሳ ዓመት በላይ ነው። በርካታ ሰዎች ሳይጋቡ ለብዙ ዓመታት አብረው ይኖራሉ። በየዓመቱ 10,000 የሚጠጉ ባለትዳሮች ፊቺ ይፈፅማሉ። ይህም በየዓመቱ ከሚጋቡት ግማሽ ያህል እንደ ማለት ነዉ። 4ዐ በመቶ የሚጠጋው የኖርዌይ ህዝብ የሚኖረው ለብቻው ነው።

መረጃ

ቤተሰብ

የኖርዌይ ህዝብ በአብዛኛው ቤተሰብ አለው። አንዳንድ ሰዎች ከሌሎች የቤተሰብ አባላት ጋር ሲኖሩ ሌሎች ደግሞ ለብቻቸው ይኖራሉ። ብቻቸውን የሚኖሩት ሰዎች በአብዛኛው ቤተሰብ ኖሯቸው ግን ቤተሰቦቻቸው ምናልባትም በሌላ ቤት፣ በሌላ ከተማ ወይም በሌላ ሃገር የሚኖሩ ይሆናሉ።

(አብሮ ኗሪ) ቤተሰብ

በአንድ ቤት ውስጥ በጋራ ኢኮኖሚ እየተዳደሩ የሚኖሩ ሰዎች ቤተሰቦች ይባላሉ። ቤተሰብ አንድ ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ ሰዎችን ያቀፈ ሊሆን ይችላል። በአሁኑ ጊዜ በአማካኝ የአንድ የኖርዌይ ቤተሰብ አባላት ብዛት ከሁለት ትንሽ ከፍ ያለ ነው።