ልጅና ቤተሰብ

የልጅነት ግዜ፣ የልጆች ህግና የልጆች መብት ጥበቃ

አምስት ልጆች አንድ ላይ በጨዋታ ላይ ያሉ ልጆች በክረምት የሚጫወቱ ልጆች

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የልጆች መብቶች ስምምነት ሁሉም ልጆች ሊከበርላቸው የሚገቡ 42 መብቶችን ይደነግጋል። ይህ ስምምነት የፀደቀው በ1989 ሲሆን ኖርዌይ ስምምነቱን የፈረመችው በ1991 ነው።
ኖርዌይ የምትገለገልበት የልጆች ህግ አላት። ህጉ ተግባራዊነቱ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ ለሁሉም ልጆችና ወጣቶች ሲሆን፥ ወላጆች ለልጆች ያላቸው ኃላፊነቶች ወይም ግደታዎች እና ልጆች ከወላጆች ሊያገኟቸው ስለሚገቡ መብቶች በዝርዝር አስቀምጧል።

አንዳንድ አስፈላጊ የሆኑ የህፃናት ህጎች

  • አንድ ልጅ ሲወለድ ሀኪም ወይም አዋላጅ አንድ ሰው መወለዱን ለመዘጋጃ ቤት መልእክት መላክ አለበት። የህፃኑ አባትና እናትም ማን እንደሆኑ ማገለፅ ያለበት ሲሆንና እናትና አባትም አብረው ስለመኖራቸውና ስለ አለመኖራቸውም አብሮ ይገለፃል። አንድ ህፃን ሀኪም በሌለበት ወይም እናት ከሀገር ውጭ ከሆነች ይህን ጉዳይ የማሳወቅ ግዴታ አለባት።
  • እንደተለመደዉ ወላጆች ለልጆቻቸው ዋና ሃላፊነት ያለባቸዉ ሲሆን ልጆች ደግሞ ከቤተሰቦቻቸዉ ፍቅርና እንክብካቤ ማግኘት ይገባቸዋል።
  • ወላጆች ልጆችን የመንከባከብ ግዴታ አለባቸው። ይህም ሲባል ለልጆቻቸው እንደ ምግብ፣ ልብስና አንዳንድ ነገሮች ለጥሩ ህይወት አስፈላጊ የሆኑትን ሟሟላት አለባቸው። ይህም የማሳደግ ግዴታ ልጆች 18 አመት እስኪሆናቸው ድረስ የሚያገለግል ነው። ልጆች 18 አመት ቢሞላቸውም ወላጆች ለልጆች የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እስኪያጠናቅቁ ድረስ የማሳደግ ግዴታ አለባቸው።
  • ወላጆች ለልጆቻቸው ጥሩ አስተዳደግና ሁል ግዜም ስለ ልጆቻቸው ምኞትና ፍላጎት ማሰብ አለባቸው። በልጆች አስተዳደግ ወቅት ልጆችን መቅጣት የልጆች ህግ ይከለክላል። ማንኛውም አደገኛ ማሰቃየት ወይም ቅስም መስበር በህግ የሚያስቀጣና የልጆች መብት ጥበቃ ቢሮ በወላጆች መካካል ሊገባ ይችላል።
  • ልጆች ለራሳቸዉ ለመወሰን እስኪችሉ ድረስ ወላጆች ስለልጆቻቸዉ የመወስን መብትና ግዴታ አለባቸዉ። በልጆች ህግ ደንብ መሰረት ልጆች እድሜያቸዉ በጨመረ ቁጥር በቤተሰብ ተሰሚነት እያገኙ መሄድ አለባቸዉ። ልጆች ስያድጉና እየበሰሉ ሲሄዱ የራሳቸዉን ጉዳይ የመወሰን መብታቸዉ እየሰፋ ይመጣል። አንድ ዕድሜዉ 7 ዓመት የሞላ ልጅ እሱን በሚመለከት ጉዳይ ላይ ቤተሰብ ሲወስን የራሱን ሃሳብ የመገለፅ መብት አለዉ። ህጉ እንደሚለዉ አንድ ልጅ ዕድሜዉ 12 ዓመት ሲሆነዉ የሚለዉ የበለጠ ተሰሚነት ያገኛል።
  • አንድ ዕድሜዉ 15 ዓመት የሞላዉ ልጅ ስለትምህርቱ እና ድርጅቶች ዉስጥ መግባትም ሆነ መዉጣት የመወሰን መብት አለዉ። ይህም ማለት የትኛዉ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እንደሚሄድ አንድ ልጅ ራሱ ይወስናል። ወላጆችና ልጅየው ስለዚህ ጉዳይ ይነጋገራሉ ብዙም ጊዜ ቤተሰቦች በእንደዚህ አይነት ጉዳይ ላይ ለልጆቻቸው ምክር ይሰጣሉ። ይሁን እንጅ የሚወስኑት ወጣት ልጆች እራሳቸው ናቸው። ወጣት ልጆች እራሳቸው በፖለቲካ ድርጅት ውስጥ መሳተፍና በሀይማኖታዊ ወይም በሌላ ማህበሮች የመሳተፍ መብት አላቸው።
  • ልጆች የመጀመሪያ ደረጀ ትምህርታቸውን እንደሚከታተሉ ቤተሰቦች የመካታተል ሀላፊነትና የልጆችን ችሎታና ፍላጎት የሚያመዛዝን ትምህርት መሆኑን መከታተል አለባቸው።
  • ምንም እንኳን ቤተሰቦቻቸው ለየብቻቸው ቢኖሩም ልጆች ከሁለቱም ቤተሰቦቻቸው ጋር የመሆን መብት አላቸው።
  • ኖርዌይ ዉስጥ የአካለ-መጠን ዕድሜ 18 ዓመት ነው። ይህ ማለት አንድ ልጅ 18 ዓመት ሲሞላው ህጋዊ ውሎችን መፈራረምና በራሱ ገንዘብ ላይ የማዘዝ መብት ይኖረዋል። ከዚህ በኋላ ወላጆች ልጃቸዉን በተመለከተ በኃላፊነት አይጠየቁም።

የልጆች መብት ጥበቃ ቢሮ

የልጆች መብት ጥበቃ ቢሮ በኖርዌይ
ከሁሉ አስቀድሞ ለልጆች እንክብከቤና አስተዳደግ ቤተሰቦች ሀላፊነት አለባቸው። ወላጆች ለምሳሌ በተለያየ ምክንያት ከባድ በሆነ የህይወት ጊዜ ለአጭር ወይም ለረጅም ጊዜ እርዳታ ሊፈልጉ ይችላሉ። በእንደዚህ አጋጣሚዎች የልጆች መብት ጥበቃ ቢሮ ከወላጆችና ከልጆች ጎን ሊቆም ይችላል።
እያንዳንዱ ወረዳ የራሱ የሆነ የልጆች መብት ጥበቃ ቢሮ አለው።

የልጆች መብት ጥበቃ ቢሮ አገልግሎቶች ስራም በልጆች መብት ጥበቃ ህግ ይተዳደራል። ይህም ህግ በኖርዌይ ለሚኖሩ ለሁሉም ልጆች የሚሰራ ሲሆን፣ ልጆችን ክየት እንደመጡ፣ የየት አገር ተወላጅ ወይም ዜግነት እንደሆኑ ሳይለይ ይረዳል።

ለልጆች የተሻለ ነገር
ለልጆች ጥቅም ሲባለ የልጆች መብት ጥበቃ ለልጆች እርዳታ ይሰጣል። ይህም ከተባበሩት መንግስታት የህፃናት መብቶች ድንጋጌ ጋር በመተባበር የሚሰራ ሲሆን የኖርዌይ አገር ህግም አንድ አካል ነው። የህፃናት መብቶች ድንጋጌም እንደሚገልፀው አንድ ልጅ እንደ ማንኛውም ሰው የመኖር፣ የማደግ፣ መጠለያ የማግኘትና የተለያዩ ነገሮች ውስጥ ተሳትፎ ከማድረግም አልፎ የተለየ እንክብካቤ የሚሻ ነው።

የልጆች መብት ጥበቃ ቢሮ አስፈላጊ ስራዎች
– መርዳትና ድጋፍ መስጠት

ልጆች ቤት ዉስጥ ወይም በሌላ ሁኔታ በሚከሰት ችግር ሲገጥማቸዉ የልጆች መብት ጥበቃ አገልግሎት ድጋፍ ይሰጣል። የሚሰጠዉ ድጋፍ ምክር፤ አመራር ወይም በእረፍት ጊዜ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ማሳተፍ፤ መዋለ ህፃናት ወይም ከትምህርት ጊዜ በሗላ በሚደረጉ ማቆያ ቦታ ማጫወት ሊሆን ይችላል። በግምት ከ10 ዉስጥ 9 የሚሆነዉ የዚህ ቢሮ አገልገሎት ቤተሰብ በፍላጎት ቤት የሚያገኘዉ ድጋፍ ነዉ።

-ጣልቃ የመግባት ሃላፊነት፤ ምናልባት ያለ ቤተሰብ ፍላጎት።

ለልጆች እንደሚታወቀዉ ቤታቸዉ ማደግ ከሁሉ የላቀ ነዉ። ነገር ግን በፍላጎት ልጆች ቤት ዉስጥ የሚያገኙት ድጋፍ በቂ ሆኖ ካልተገኘ የልጆች መብት ጥበቃ አገልግሎት ጣልቃ የመግባት ሃላፊነት አለበት። የልጆች መብት ጥበቃ አገልግሎት ልጅን የማሳደጉን ሃላፊነት ከቤተሰብ የሚቀበለዉ በጣም አሳማኝ ጉዳይ ሲኖር ነዉ። የዚህም ምሳሌ ልጆች የማሳደግ እንክብካቤ ጉድለት ሲታይ፤ ለምሳሌ ማጉላላት። ያለ ቤተሰብ ፍቃድ ልጆች ከቤተሰብ ዉጪ እንዲኖሩ ለማድረግ ፍርድ የመስጠት ሥልጣን ያለዉ የዞኑ የልጆችና ማህበራዊ ጉዳይ ኮሚቴ መበየን አለበት።

የልጆች መብት ጥበቃ አገልገሎት ጉዳይ አፈፃፀም
ብዙ የልጆች መብት ጥበቃ አገልግሎት ጉዳዮች የሚጀመሩት ቤተሰብ ራሱ እርዳታ ለማግኘት የልጆች መብት ጥበቃ አገልግሎት ቢሮን በመጠየቅ ነዉ። የልጆች መብት ጥበቃ አገልግሎት ቢሮ ከሌሎች እንደ ጤና ጣቢያ፤ ሆስፒታል፤ ትምህርት ቤት፤ መዋለ ህፃናት ጎረቤትና ከሌሎች ለልጆች ስጋት ከገባቸዉ አካላት ጥቆማ ያገኛል። ማንኛዉም በመንግስት መስሪያ ቤት የሚሰራ እንደ ጤና ጣቢያ፤ ትምህርት ቤትና መዋለ ህፃናት ያሉት ለልጆች አስጊ ጉዳይ ሲመለከቱ ለየልጆች መብት ጥበቃ አገልግሎት የማሳወቅ ግዳጅ አለባቸው። ሁሉም የልጆች መብት ጥበቃ አገልግሎት ጋር የሚደርሱ ጉዳዮች ይገመገማሉ። የልጆች መብት ጥበቃ አገልግሎት አሳማኝ ጉዳይ ካገኘ ቤተሰብንና ልጆችን በማነጋገር የልጆችን ሁኔታ ያጤናል።

እንዴት ልጆችና አዋቂዎች የልጆች መብት ጥበቃን አገልገሎትን ቢሮ ማግኘት ይችላሉ?
ሁሉም ወረዳዎች ቀን ክፍት የሚሆን የልጆች መብት ጥበቃ አገልግሎት ይኖራቸዋለ። ማታና በ እረፍት ቀናት ለልጆች የሚያሰጋ ሁኔታ ሲገጥም የልጆች የድንገተኛ ሁኔታ ስልክ 116111 መደወል ይቻላል።

መረጃ

የልጆች ድጋፍ ክፍያ

የልጆች አበል ዓላማው በኖርዌይ የሚኖሩ ከ18 ዓመት እድሜ በታች ያሉ ልጆችን በገንዘብ ለመደገፍ ሲሆን፣ ለልጆች ያሎትን ወጪዎች ለመሸፈን ይውላል። የልጆች አበል በክሮነር ምን ያህል እንደሆነ እና ሌሎች መረጃዎችን ለማወቅ NAV Barnetrygd ድረ-ገጽ ይመልከቱ።

መዋለ ህፃናት ለማይሄዱ ልጆች ክፍያ

መዋለ ህፃናት ለማይሄዱ ልጆች ክፍያ የሚሰጠው እድሜያቸው 1 እስከ 2 ዓመት ለሆኑትና መዋለ ህፃናት ለማይሄዱ ልጆች የሚከፈል የኢኮኖሚ ድጋፍ ነው። ይህም ክፍያ ከ13 እስከ 18 ወራት ለሆኑት ልጆች በወር 5000 ክሮነር ሲሆን የተወሰነ ሰዓት መዋለ ህፃናት ለሚቆዩ ልጆች ይህ ክፍያ ይቀነሳል።፡NAV Kontantstøtte.