የተለያዩ መኖሪያዎች
ኖርዌይ ውስጥ ከሁለት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የመኖሪያ ቤቶች አሉ። ከእነዚህ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ለአንድ ቤተሰብ የሚሆኑ ቪላ ቤቶች ናቸው። እንደ ኦስሎ ባሉ ትልልቅ ከተሞች ውስጥ 7ዐ በመቶ የሚሆኑ የመኖሪያ ቤቶች የሚገኙት አፓርታማዎችና ባለፎቅ ህንፃዎች ላይ ነው። በትናንሽ ወረዳዎች (ኮሚዩነ) ደግሞ እስከ 9ዐ በመቶ የሚደርሱት ቤቶች ለአንድ ቤተሰብ የሚሆኑ ቪላዎች ናቸው። ወደ አንድ-አራተኛ የሚጠጋው ህዝብ ቤት ተከራይቶ የሚኖር ሲሆን፣ ሌሎቹ ግን የራሳቸው መኖሪያ ቤት አላቸው።
ነዋሪዎች የመኖሪያ ቤት በሁለት መንገዶች ሊኖራቸው ይችላል። የመጀመሪያው የግል የመኖሪያ ቤት ባለቤትነት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በቤት ማህበራት ወይም በአክስዮን አማካይነት የቤት ባለቤት መሆን ነው።
ኖርዌይ ውስጥ የሚገኙ ሁሉም የመኖሪያ ቤቶች ማለት ይቻላል የራሳቸው የሆነ የመታጠቢያና የመፀዳጃ ክፍል እንዲሁም የምግብ ማብሰያ ክፍል አላቸው።