ልጅና ቤተሰብ

በራስ ሕይወት ላይ የመወሰን መብት

በቤተሰብ ውስጥ፣ በፍቅረኛሞች መካከል፣ አብረው በሚኖሩ ጥንዶች እና በባለትዳሮች መካከል የሚከሰተውን ጨምሮ ማንኛውንም ዓይነት ጥቃት ኖርዌይ ውስጥ በህግ የተከለከለ ነው።

በልጆች አካል ላይ የሚደርስ ቅጣት፣ የሴት ልጅ ግርዛት እና አንድን ሰው ያለፈቃዱ እንዲያገባ ማስገደድ እንደ ጥቃት ይቆጠራል።

በቅርብ ሰዎች መካከል ስላለ ጥቃት የበለጠ መረጃ ከዚህ ድረ-ገፅ ማግኘት ይቻላል፡ www.kompetansenorge.no/vold.

መረጃ

ማሰቃየት ምንድነው?

  • ማሰቃየት ሌሎች ላይ በደል ማድረስ ነው።
  • ምሰቃየት ሌሎች ሰዎች ላይ ጉዳት፣ ህመም ወይም ፍራቻ የመፍጠር ተግባር ነው።
  • ማሰቃየትም በአካልና በአእምሮም ልሆን ይችላል።

በሚቀራረቡ ሰዎች መካከል የሚፈጠር ማሰቃየት ማለት ጉዳት የሚያደርሰውም ሆነ የሚደርስበት ሰው ቤተሰብ፣ ጓደኛ ወይም የሚደጋገፉ ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ።

UDI eller politiet