ጤና

ታሪካዊ እድገት

ዛሬ ኖርዌይ ውስጥ ያለው የኑሮ ደረጃ ከፍተኛ ነዉ። ለተለያዩ ከባድ ህመሞች ህክምና የሚሆኑ መድሃኒቶች ከመኖራቸውም በተጨማሪ የማህበራዊ ዋስትና ሥርዓቱ እያንዳንዱ ሰው የህክምና አገልግሎትና መድኃኒቶች ማግኘት የሚችልበትን ሥርዓት ዘርግቷል። ልጆችን በርካታ በሽታዎች ለመከላከል የሚረዳ የነፃ ክትባት ይሰጣቸዋል።

ባለፉት ረጅም ዓመታት ውስጥ በርካታ ለውጦች በመኖራቸው የሰዎች የዕድሜ ጣሪያ ግምት አሁን በጣም ጨምሯል። በ19ዐዐ አካባቢ የተወለደ ሰው በህይወት ይኖራል ተብሎ የሚጠበቀዉ የዕድሜ ጣሪያ 55 ዓመት ገደማ ነበር። በ195ዐ የተወለደች አንድ ሴት ልጅ ትኖራለች ተብሎ ይጠበቅ የነበረው የዕድሜ ጣሪያ 73 ዓመት ከስድስት ወር ሲሆን፣ ወንድ ልጅ ደግሞ 7ዐ ዓመት የዕድሜ ጣሪያው ነበር። በ2ዐ17 ግን የሴት ልጆች የዕድሜ ጣሪያ 84 ሲሆን፣ ለወንዶች ደግሞ 8ዐ ዓመት ነው።

ባለፉት ክፍለ ዘመናት የታዩ የዕድሜ ጣሪያ ዕድገቶች፡

መረጃ

«ባለፉት 100 ዓመታት ውስጥ የእድሜ ጣራው በአንድ ትውልድ ያህል ጨምሯል!» (የንስ ስቶልተንበርግ፣ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር)

Jens Stoltenberg, (fotograf: Bjørn Sigurdsøn, Scanpix/SMK)