ጤና

የተለያዩ የጤና እንክብካቤ አገልግሎቶች

የግል ሐኪም የማግኘት አገልግሎት

ሁሉም ነዋሪዎች የጠቅላላ ሕክምና የሚሰጥ የግል ሐኪም የማግኘት መብት አላቸው። አንድ ሰው ሲያመው በመጀመሪያ ምርመራ የሚያደረግለት ይህ ሐኪም ነው። የግል ሐኪሙ ከሌሎች በፊት የራሱን ታካሚዎች የመርዳት ግዴታ አለበት። ይህ የግል ሐኪም ታካሚው የስፔሻሊስት ህክምና ሲያስፈልገው ወደ ሌላ ሐኪም ይመራዋል። የግል ሐኪም ለመቀየር ወይም በሌሎች የጤና ጉዳዮች ላይ መረጃ ለማግኘት የሚተለውን ድረ-ገፅ ይጐብኙ፡https://helsenorge.no

የግል ሐኪም የታካሚዉን ሚስጥር የመጠበቅ ኃላፊነት ስላለባቸዉ ከታካሚው ፈቃድ ውጭ ሐኪሙና ታካሚው የተወያዩትን ለሌላ ሰው መናገር አይችልም።

የመድኃኒት መሸጫ መደብር

የመድኃኒት መሸጫ መደብር መድሃኒቶችን ከመሸጥ በተጨማሪ ስለጤና እና ስለመድሃኒቶች አጠቃቀም ምክር ይሰጣል። ብዙ መድሃኒቶች የሚገዙት ከመድሃኒት መሸጫ መደብር (ፋርማሲ) ነው። ቀላል የህመም ማስታገሻዎችን የመሳሰሉ አንዳንድ መድሃኒቶችን ከሸቀጣ ሸቀጥ መሸጫ መደብር ወይም ከነዳጅ ማደያ ሱቆች መግዛት ይቻላል። የመድሃኒት ዋጋ ከፋርማሲ ፋርማሲ ወይም ከሱቅ ሱቅ ሊለያይ ይችላል።

ብዙ መድሃኒቶች የሐኪም ማዘዣ ያስፈልጋቸዋል። ይህ ማለት በቅድሚያ ሐኪምዎን ሳያማክሩ መድሃኒቶቹን መግዛት አይችሉም። ሐኪምዎ የመድሃኒቱን ዓይነትና እንዴት መውሰድ እንዳለበዎት የሚገልፅ ማዘዣ ይሰጥዎታል።

በሰማያዊ ማዘዣ የሚገዙ መድሃኒቶች

ከባድ እና የረጅም ጊዜ ህመም ካለቦት መድሃኒቶች፣ ምግብ ነክ ነገሮች እና የህክምና ቁሳቁሶችን በ ፟ሰማያዊ ማዘዣ ̋̋ መግዛት ይችላሉ። ሰማያዊ ማዘዣ ከያዙ የመድሃኒቱን ሙሉ ዋጋ አይከፍሉም። እርስዎ የሚከፍሉት የተጠቃሚ የክፍያ ድርሻ ብቻ ሲሆን አብዛኛውን ወጪ የሚሸፍነው መንግሥት ነው።

በሰማያዊ ማዘዣ መድሃኒቶችን ሲገዙ እና የግል ሐኪም አገልግሎት ሲያገኙ የሚከፍሉት የተጠቃሚ የክፍያ ድርሻ በሙሉ ይደመርና መጠኑ ታይቶ የነፃ የህክምና ካርድ ሊሰጦት ይችላል።

የጥርስ ሃኪም

ልጆች ዕድሜያቸው 18 ዓመት እስኪሞላቸው መደበኛ የጥርስ ህክምና ክትትል ይደረግላቸዋል። ወጪዉን የሚሸፈነው መንግሥት ነው። ከ18 እስከ 2ዐ ዓመት ያሉት ወጣቶች 25 በመቶ የጥርስ ህክምና ወጪ ሲከፍሉ መንግሥት 75 በመቶውን ይሸፍንላቸዋል። ከ2ዐ ዓመት በላይ የሆኑ አዋቂዎች ግን ሙሉውን ወጪ ራሳቸው ይከፍላሉ። አዋቂዎች በግል የሚሰሩ የጥርስ ሃኪሞችን ራሳቸው ፈልገው ማግኘት አለባቸው። በዓመት አንድ ጊዜ የጥርስ ምርመራ ማድረግ የተለመደ ነው።

Egenandel hos tannlege for ungdom 18-20 år

ልጆች ወይም ወጣቶች የጥርስ ማስተካከያ አምባር ካስፈለጋቸው ወላጆች በቅድሚያ ለኢንሹራንስ የሚከፈለውን ወጪ መሸፈን አለባቸው።

የጥርስ ማስተካከያ አምባር ያደረገች ልጅ

ሆስፒታል ተኝቶ መታከም

በመንግሥት ሆስፒታል ተኝቶ የሚታከም ሰዉ ህክምና የሚያገኘው በነፃ ነዉ። ሁሉም የህክምና ወጪዎች እንዲሁም የአልጋና የምግብ አገልግሎት ወቀጠሮጪ የሚሸፈነው በመንግሥት ነው።

እርስዎ በሆስፒታል ተኝተዉ ለመታከም አስቀድመዉ ካሰቡ የሚታከሙበትን ሆስፒታል መምረጥ ይችላሉ። ህክምና ለማግኘት የተለያዩ የቀጠሮ ጊዜዎች አሉ። የሚከተለውን ድረ-ገፅ ይመልከቱ፡-.

ኖርዌይ ውስጥ ጥቂት የግል ሆስፒታሎችም አሉ። በግል ሆስፒታሎች መታከም ከፈለጉ ለህክምናው መክፈል ይኖርብዎታል።

የሆስፒታል የተመላላሽ ህክምና ክሊኒክ

የተመላላሽ ህክምና ማለት ሆስፒታል ውስጥ አልጋ ሳይዙ የሚሰጥ ህክምና ነው።ተመላላሽ ታካሚ ከሆኑ በቀጠሮ ሰዓት ሆስፒታል መጥተዉ ህክምና ካገኙ በኋላ ወደ ቤትዎ ይመለሳሉ ማለት ነው። እርስዎ ተመላላሽ ታካሚ ከሆኑ ልክ ለጠቅላላ ሃኪም ወይም ለስፔሻሊስት ሃኪም እንደሚከፍት ሁሉ የተጠቃሚ የክፍያ ድርሻ መክፈል ይጠበቅብዎታል።

ስፔሻሊስት ሃኪም

ስፔሻሊስት ሃኪም ብለን የምንጠራቸው ለምሳሌ የማህፀን ሐኪም፣ የቆዳ ሐኪም፣ የአንገት በላይ (የጆሮ፣ የአፍንጫ እና የጉሮሮ) ሐኪም ወይም የልጆች በሽታዎችን ጠልቀው በማጥናት የሰለጠኑ ሐኪሞች ናቸው።

በስፔሻሊስት ሃኪም ለመታየት በመጀመሪያ ከግል ሃኪምዎ ወይም ከሌላ ጠቅላላ ሃኪም ሪፌራል ሊኖሮት ይገባል። ይህ ካልሆነ ግን ከፍተኛ የተጠቃሚ የክፍያ ድርሻ መክፈል ይኖርብዎታል።

አምቡላንስ

የአምቡላንስ አገልግሎት ከፈለጉ በ113 ላይ ይደውሉ። ከዚያም የአምቡላንስ አገልግሎት ከሚሰጠው ክፍል ጋር ያገናኙዎታል። የአምቡላንስ አገልግሎት ሲያስፈልግዎ ትክክለኛውን መረጃ መስጠት አስፈላጊ ነው። እነዚህም፡-

ማንነትዎን
(ስም፣ ስልክ ቁጥር፣ ከየት እንደሚደውሉ)

ምን እንደተከሰተ
(ምን ያህል ሰዎች እንደተጐዱ፣ የጉዳቱ ክብደት ወዘተ.)

የት እንደሚገኙ
(ትክክለኛ አድራሻ ወይም የቦታ አገላለጽ)

ድንገተኛ ክፍል

የግል ሐኪሞ ከሚሰራበት ሰዓት ውጭ አስቸኳይ ህክምና ሲያስፈልግዎ የድንገተኛ ክፍል አገልግሎትን በ(116 117) ደውለው ማግኘት ይችላሉ።

ኖርዌይ ውስጥ የሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች (ኮሚዩነ) የድንገተኛ ህክምና አገልግሎት አላቸው። ድንገተኛ ክፍሎች ከሐኪም ቤቶች ሥራ ሰዓት ውጭ በምሽት፣ በሌሊት፣ ቅዳሜና እሁድ ክፍት ናቸው። በድንገተኛ ክፍል ለመታከም የተጠቃሚ የክፍያ ድርሻ መክፈል ይኖርብዎታል። ለህክምና ቁሳቁስ፣ ለናሙና እና ለመሳሰሉት ደግሞ ተጨማሪ ክፍያ ይኖራል።

በአቅራቢያዎ የሚገኘው የድንገተኛ ጊዜ አገልግሎት የትኛው እንደሆነ እንዲያውቁ ይመከራሉ!

መረጃ

የተጠቃሚ የክፍያ ድርሻ

  • የህክምና ወጪን አብዛኛውን የሚሸፍነው መንግሥት ነው። ታካሚው የተጠቃሚ የክፍያ ድርሻውን ሲከፍል የተቀረውን መንግስት ይከፍላል።
  • ታካሚ ከተጠቃሚ የክፍያ ድርሻ ባሻገር ለመጠቅለያ፣ ለመርፌ፣ ለመድኃኒት፣ ለላቦራቶሪ ምርመራ እና ለመሳሰሉት መክፈል ይኖርበታል።
  • ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች የተጠቃሚ የክፍያ ድርሻ መክፈል አይጠበቅባቸውም። የቅድመ ወሊድ የእርግዝና ክትትልም እንዲሁ በነፃ ነው።
  • የግል ሀኪምጋ (ፋስትሌገ) አብዛኛውን ጊዜ የተጠቃሚ የክፍያ ድርሻ ከ150 እስከ 300 ክሮነር ይደርሳል።

የነፃ ህክምና ካርድ

በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የከፈሉት የተጠቃሚ የክፍያ ድርሻ ድምሩ የተወሰነ መጠን ሲደርስ የነፃ የህክምና ካርድ የማግኘት መብት አለዎት። ይህንን የገንዘብ መጠን በአንድ ዓመት ውስጥ እንደከፈሉ ከኖርዌይ የጤና ምጣኔ ሃብት አስተዳደር (HELFO) የነፃ ካርድ ወዲያውኑ በፖስታ ይደርሶታል። ከዚያም ዶክተሩጋ ሲቀርቡ ወይም ደግሞ መድኃኒት በ”ሰማያዊ የማዘዣ ወረቀት” ሲገዙ የነፃ ካርዱን ማሳየት አለቦት። በዚህ መልኩ የነፃ ካርዱን ያገኙበት ዓመት መጨረሻ ድረስ የተጠቃሚ የክፍያ ድርሻ መክፈል አይጠበቅቦትም።

ለበለጠ መረጃ: https://helsenorge.no