ጤና

የዕድሜ ባለፀጋዎችና ጤና

ኖርዌይ ውስጥ ሁሉም በዕድሜ የገፉ ሰዎች የጡረታ አበል ያገኛሉ። የጡረታው መጠን የሚወሰነው ቀድሞ በነበራቸው የስራ ገቢ መሰረት ነው።

አብዛኞቹ የኖርዌይ ነዋሪዎች የሚኖሩት በራሳቸው የመኖሪያ ቤት ነው።አንዳንዶቹ የተለያዩ ድጋፎችን ለምሳሌ የቤት ውስጥ የህክምና እንክብካቤ፣ የቤት ውስጥ እርዳታ፣ በወረዳዉ በሚገኙ የአረጋዊያን ማቆያ ማዕከሎች አገልግሎት ማግኘት ወዘተ. በወረዳዉ (ኮሚዩነ) አማካይነት ይሰጣቸዋል። ብዙዎቹ ራሳቸውን ያስተዳድራሉ ወይም በቅርብ በዘመዶቻቸው ይታገዛሉ።

En eldre dame får medisinsk hjelp
በዕድሜ የገፉ ሰዎች ራሳቸውን መርዳት የማይችሉበት ደረጃ ላይ ሲደርሱ ወደ አረጋዊያን ማቆያ ሊወሰዱ ይችላሉ። ግን ዕድሜያቸው ከ9ዐ ዓመት በላይ ከሆኑ አረጋዊያን መካከል ግማሽ የሚሆኑት ብቻ አረጋዊያን ማቆያ ይኖራሉ።

የቤት ውስጥ እንክብካቤና ድጋፍ የሚሰጣቸው አረጋዊያን ለአገልግሎቱ የተጠቃሚ የክፍያ ድርሻ ይከፍላሉ። ቀሪውን ክፍያ የሚሸፍነው ወረዳዉ (ኮሚዩነ) ነው። ተገልጋዩ የሚከፍለው የገንዘብ መጠን እንደየወረዳዉ ይለያያል።

በአረጋዊያን ማቆያ የሚኖሩ በዕድሜ የገፉ ሰዎችም የተጠቃሚ የክፍያ ድርሻ ይከፍላሉ። በእነዚህ ማቆያዎች መኖር በዓመት እስከ 8ዐዐ,ዐዐዐ ክሮነር የሚደርስ ወጪ ይጠይቃል። የተጠቃሚ የክፍያ ድርሻ መጠን የሚወሰነው በተጠቃሚው ገቢ መሠረት ነው።

Eldre person i rullestol Eldre mann på sykehjem

አረጋውያን ብዙ ጊዜ ልዩ የጤና ችግር ያጋጥማቸዋል።

  • ወደ 100,000 አካባቢ የሚጠጉ አረጋውያን ኖርዌይ ውስጥ በዱባቴ ይሰቃያሉ። ምክንያቱ ደግሞ ጤና ማጣት ወይም ብቸኝነትና ራስን የማግለል ሊሆን ይችላል። የአረጋውያን የማስታወስ ችሎታ ማነስ እና እንዲሁም በአብዛኛዎቹ የአእምሮ መሳት መኖር የተለመደ ነው። የአእምሮ መሳት ማለት የአዕምሮ መጎዳት እና እንዲሁም የማስታወስ ችሎታ፣ የስሜታዊነትና የማህበራዊ ግንኙነት ችሎታ መጎዳት ማለት ነው።
  • አንዳንድ ሰዎች ሲያረጁ የምግብ ፍላጐታቸው ይቀንሳል። ሰውነታቸው የምግብ ጉድለት ወይም የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ያጋጥመዋል። በመሆኑም በሽታን የመቋቋም አቅማቸው ስለሚደክም ለበሽታና ለኢንፌክሽን በቀላሉ ይጋለጣሉ።

መረጃ

የህዝብ ጤንነት

የህዝብ ጤንነት ባለፉት 100 ዓመታት በጣም የተሻለ ሆኗል። ይህም ምክንያቱ የኅብረተሰብ ዋስትናዉ በደንብ በማደጉ ለህዝቡ የተሻለና የተረጋጋ ኑሮ ለመኖር እድል በመስጠቱ ነው።
የኖርዌይ ህዝብ ከበፊቱ ይልቅ ዛሬ ረጅም እድሜ ይኖራል። ብዙ አረጋውያንም እንዲሁ ከበፊቱ የበለጠ ጤናማ ናቸው። ይህም ንቁና ጥሩ ህይወት ለረዘመ ጊዜ እንዲኖሩ ይረዳል።