የሥራ አለም መብቶችና ግዴታዎች
ኖርዌይ ውስጥ የሥራ ህይወት በተለያዩ ህጐችና ውሎች ይመራል። ለምሳሌ የኖርዌይ የሥራ አካባቢ ድንጋጌ እና የእረፍት ጊዜ ድንጋጌ ተጠቃሽ ናቸው።
የተወካዮች ምክር ቤት ፖለቲከኞች ህጐቹን የሚያፀድቁ ሲሆን፣ አሰሪዎችና ሠራተኞች ደግሞ በማህበራቸው አማካይነት ከስምምነት ላይ ይደርሳሉ።
ህጎቹ በሁሉም ቀጣሪዎችና ተቀጣሪዎች ላይ ተግባራዊ ሲደረጉ፣ ዉሎቹ ደግሞ የሚያገለግሎት ለተወሰኑ ሙያዎች ነው።
በህግ የፀደቁ መብቶች ምሳሌዎች፡-
- ኖርዌይ ውስጥ ሁሉም ሠራተኞች የቅጥር ውል የመፈራረም መብት አላቸው። ይህ ውል ሊያካትት ከሚገባቸው መረጃዎች መካከል የሠራተኛው ደሞዝና እና የሥራ ሰዓታት ይገኙበታል።
- ኖርዌይ ውስጥ መደበኛው የሥራ ጊዜ በሣምንት 37.5 ሰዓታት ነው።
- ኖርዌይ ውስጥ ሠራተኞች በየዓመቱ ቢያንስ 25 የሥራ ቀናት እረፍት ማግኘት ይችላሉ።
- ኖርዌይ ውስጥ ሠራተኞች ራሳቸዉ ከታመሙ ወይም ልጆቻቸው ህመም ካጋጠማቸው ሙሉ ክፍያ እያገኙ ለተወሰኑ ቀናት ከሥራ መቅረት ይችላሉ።
- ሠራተኞች የወሊድ ፈቃድ ከነደሞዙ የመውሰድ መብት አላቸው።
- ሠራተኞች ሥልጠና ሲወስዱ ደሞዝ የማግኘት መብት አላቸው።