የስራ ህይወት

ድርጅቶችና አብሮ መወሰን

የሥራ ማህበራት

  • ሠራተኞችና አሠሪዎች የየራሳቸው ማህበራት አሏቸው። በጣም ትልቁ የሠራተኞች ማህበር ኤል ኡ ሲባል፣ ትልቁ የአሰሪዎች ማህበር ደግሞ ኤን ሆ ኡ ይባላል። የእነዚህ ማህበራት ሥራዎች የደሞዝ እና የሥራ ሰዓት ስምምነት ማድረግን ያካትታል።
  • አሠሪዎችና ሠራተኞች በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ሲስማሙ ውል ይፈረማል። እነዚህ ዉሎች በህጋዊነት የሚያገለግሉት በአብዛኛው ለሁለት ዓመታት ሲሆን፣የጋራ ስምምነቶች ተብለዉ ይጠራሉ። ሠራተኞችና አሰሪዎች ስምምነቶቹን የማክበር ግዴታ አለባቸው።
  • ኖርዌይ ውስጥ ለሠራተኞች ጥቅም መብት የቆሙ ማህበራት የሠራተኛ ማህበራት ተብለው የሚጠሩ ሲሆን፣ ብዙ ሠራተኞች የእነዚህ ማህበራት አባል ናቸው።
  • ሠራተኞች የማህበሩ አባል ለመሆን ክፍያ ይከፍላሉ።

በሥራ ህይወት ላይ አስተዋጽኦ ማድረግ

በሥራ ቦታ ጥሩ የስራ ሁኔታዎች ለመፍጠር ሠራተኞችና አሰሪዎች በተለያዩ ስምምነቶች ላይ ተባብረው መሥራት ይኖርባቸዋል።ስለዚህ በኖርዌያዉያን የሥራ ህይወት ውስጥ በጋራ ውሳኔ ለመወሰን እንዲቻል እና የስራ ቦታ ዲሞክራሲ እንዲሰፍን የሚያደርጉ ነገሮች ይመቻቻሉ። እያንዳንዱ ሠራተኛ ሊደመጥና ሥራውን የማመቻት ተግባር ላይ መሳተፍ መቻል አለበት። በሠራተኞች ማህበራት አማካይነት ሠራተኞች ከሚሰሩበት ድርጅት ጋር ይወያያሉ፤ ስለድርጅቱ እንቅስቃሴዎችም መረጃ ያገኛሉ።

ትልልቅ ኩባንያዎች የጤና፣ ደህንነትና አካባቢ ሥርዓት (ሆ ኤም ኤስ) በሥራ ሥፍራ እንዲኖር የማድረግ ግዴታ አለባቸው። ሥራው የሚዘጋጅው እና ክትትል የሚደርግበት በአንድ የሠራተኞች ተወካይና በአንድ የሥራ አመራር ተወካይ ይሆናል።

መረጃ

<የሠራተኞች አገር አቀፍ ድርጅት (ኤል ኦ)የሠራተኞች ድርጅት (ኤል ኦ) ትልቁ የሠራተኞች ድርጅት ነው።

የንግድ ሥራዎች ድርጅት (NHO)የንግድ ሥራዎች ድርጅት ትልቁ የሥራ ቀጣሪዎች ድርጅት ነው። Landsorganisasjonen (LO) Næringslivets hovedorganisasjon (NHO)