የስራ ህይወት

የኑሮ ዋስትና ያለው ማህበረሰብ የስራ ቦታዎችን ይፈጥራሉ።

የኖርዌይ የማህበራዊ ዋስትና ሥርዓት በአግባቡ መሥራት እንዲችል በተለያዩ ሙያዎች ላይ የተሰማሩ ሰዎች ያስፈልጋሉ።

የሚከተሉት ጥቂት ምሳሌዎች ናቸው፡-

  • <መምህራን፣ የቢሮ ሠራተኞች፣ የፅዳት ሠራተኞችና ሌሎች የትምህርት ቤት ሠራተኞች/li>
  • ሐኪሞች፣ ነርሶች፣ የጤና ረዳቶች፣ የቢሮ ሠራተኞች፣ የፅዳት ሠራተኞችና ሌሎች የሆስፒታልና የአረጋዊያን እንክብካቤ መስጫ ቤቶች ሠራተኞች
  • የሥራ ፈፃሚዎች፣ የቢሮ ሠራተኞችና ሌሎች የናቭ ሠራተኞች

በትምህርትና የጤና ጥበቃ ዘርፎች የሚሰሩ አብዛኛዎቹ ሰዎች የመንግሥት ሠራተኞች ናቸው። ስለዚህ ሥራ የሚሰሩት በማእከላዊ መንግሥት፣ በዞን ወይም ወረዳ መሥሪያ ቤቶች ዉስጥ ነው። አንዳንድ ጊዜ መንግሥት የተለያዩ አገልግሎቶችን ከግል ድርጅቶች ይገዛል። ለምሳሌ የግል ሐኪም አገልግሎት ለተጠቃሚው የሚሰጡ በግላቸው ለሚሰሩ ሐኪሞች መንግስትና ወረዳው አስፈላጊውን ክፍያ ይከፍላሉ።

መረጃ

አንድ ለህዝቡ ዋስትና የሚሰጥ ህብረተሰብ ብዙ ሰራተኞችን ይፈልጋል።

በዛሬው ጊዜ መስራት ከሚችሉት 30% የሚሆኑት የመንግስት ስራን ይሰራሉ