ስራ መፈለግ
ምንም እንኳን ኖርዌይ ውስጥ የሥራ አጥነት መጠን ዝቅተኛ ቢሆንም ክፍት ሥራ ቦታዎችን ለማግኘት ጠንካራ ውድድር ሊኖር ይችላል። ሥራ ማግኘት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ቀልጣፋ መሆን አለበት። ከሌሎች ሰዎች ጋር ያለዎትን ትውውቅ መጠቀምና ሥራ ለመሥራት ፍላጐት እንዳሎት ማሳየት አስፈላጊ ነው። በኢንተርኔት ድረ-ገፆችና በጋዜጦች ብዙ ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያዎች ይወጣሉ።
የሚፈልጉት ዓይነት የሥራ ማስታወቂያ ካዩ የሥራ ቅጥር ማመልከቻና ካሪኩለም ቪቴ (ሲቪ) በአድራሻው መላክ ይኖርብዎታል። ሲቪዎ ስለማንነትዎ፣ በምን ዓይነት ትምህርት እንደሰለጠኑ እና ምን ዓይነት የሥራ ልምድ እንዳለዎት መግለፅ አለበት። ጊዜ ወስደዉ ጥሩ የሥራ ቅጥር ማመልከቻ መፃፍ አስፈላጊ ነው። ያን ካደረጉ ምናልባት ቀጣሪው ለስራ ቃለ መጠየቅ እንዲቀርቡ ሊጠራዎት ይችላል።
ለቃለ መጠየቅ ከመሄድዎ በፊት በደንብ መዘጋጀት አለብዎት። ስለቀጣሪው ድርጅት የቻሉትን ያህል መረጃ መሰብሰብ አለብዎት። ምናልባት የድርጅቱን ድረ-ገፅ በማንበብ ወይም ድርጅቱን የሚያውቁ ሰዎችን በመጠየቅ መረጃውን ማግኘት ይቻላሉ።
በቃለ መጠየቁ ላይ የተለያዩ ጥያቄዎችን እንዴት መመልስ እንደሚገባ በደንብ ማሰብ የስፈልጋል። ቀጣሪዉ ምን ዓይነት ጥያቄዎች ሊጠይቅ ይችላል? እርስዎስ ምን ይመልሳሉ?