የስራ ህይወት

ደሞዝና ቀረጥ

ኖርዌይ ውስጥ ስለዓመታዊ ደሞዝ መናገር የተለመደ ነው። የሙሉ ሰዓት ሥራ የሚሰራ አንድ ሠራተኛ አማካይ ጠቅላላ ዓመታዊ ደሞዝ 500,000 ገደማ ነው። ሴቶች የሚከፈላቸው ደሞዝ ወንዶች በአማካይ ከሚያገኙት 85 በመቶ ያህሉን ነው። Se SSBs nettside: Lønn, alle ansatte.

በወር አንዴ በተመሳሳይ ቀን የደሞዝ ክፍያ መቀበል የተለመደ ነው። ወርሃዊ የተጣራ የደሞዝ መጠን በሠራተኛው የባንክ ቁጥር በቀጥታ ገቢ ይደረጋል። በተጨማሪም ሠራተኛው ምን ያህል የተጣራ ደሞዝ እንደተከፈለውና ምን ያህል ግብር እንደተቆረጠበት የሚገልፅ የደሞዝ ሂሳብ ደረሰኝ ይሰጠዋል።

ለሠራተኛው የተጣራ ደሞዝ ከመክፈሉ በፊት ከጠቅላላ ገቢው ላይ ግብር መቀነስ የቀጣሪው ኃላፊት ነው። ቀጣሪው ከሠራተኛው የተቀነሰውን ግብር ለመንግሥት ያስተላልፋል።

የኖርዌይ የማህበራዊ ዋስትና ሞዴል ሙሉ በሙሉ የተመሰረተው ከነዋሪዎች በሚሰበሰቡ የተለያዩ ቀረጦችና ግብሮች ላይ ነው። እነዚህ ቀረጦችና ግብሮች የማህበራዊ ዋስትና ጥቅማ ጥቅሞችን ለመደጐም ይውላሉ።ኖርዌይ ውስጥ የሚገኙ ሁሉም ሠራተኞች እና አሠሪዎች ለሚኖሩበት ወረዳ እና ለመንግሥት ግብር ይከፍላሉ።

እያንዳንዱ ሠራተኛ የሚከፍለው የግብር መጠን ይለያያል። በአጠቃላይ ግን የገቢ መጠን ከፍ ሲል የግብር መጠኑም ከፍተኛ ይሆናል። ይሁን እንጂ ለብድር የምንከፍለው የወለድ መጠን እንዲሁም ለልጆች እንክብካቤና ከሥራ ጋር ተያያዥነት ላላቸው ጉዳዮች የምናወጣው የጉዞ ወጪ ታሳቢ ተደርጐ ምን ያህል ግብር መክፈል እንዳለብን ይወሰናል። በአማካይ አንድ ሠራተኛ ከሚያገኘው ጠቅላላ ገቢ 25 በመቶ የሚሆነውን ለግብር ይከፍላል።

መረጃ

የቀረጥ ካርድ

ሥራ የሚሠራ ሁሉ የቀረጥ ካርድ ያስፈልገዋል። የቀረጥ ወረቀትን ከ Skatteetaten ማዘዝ ይችላሉ።

የደመወዝ ወረቀት

ደመወዝ የሚከፈለው ማንም ሰው የደመወዝ ወረቀት ያገኛል። የደመወዝ ወረቀትም ለቀረጥ ክፍያ ደረሰኝ ነው።

ሙሉ ደመወዝ

ይህም ቀረጥ፣ ጡረታና ሌሎች ወጪዎች ሳይቆረጡ በፊት ያለ ሙሉ ደመወዝ ነው።

የተጣራ ደመወዝ

ይህም ቀረጥ፣ ጡረታና ሌሎች ወጪዎች ከተቆረጡ በኋላ ያለ ደመወዝ ነው።