የስራ ህይወት

ጥቁር ገበያ

በጥቁር መሥራት ህገ-ወጥነት ሲሆን እንደ ኢኮኖሚያዊ ወንጀል ይታያል። አሠሪዎችና ሠራተኞች በዚህ ወንጀል በህግ ሊቀጡ ይችላሉ።

በጥቁር መሥራት የግብረ ገብ ኣልባነት ነው። ግብር የማይከፍል ሠራተኛ ለህብረቱ ምንም አስተዋፅኦ አያደርግም። ስለዚህ በጥቁር መሥራት ከሌላው የህብረተሰቡ አባል የመስረቅ ያህል ነው።

በጥቁር ሥራ ሳቢያ ከግብር ገቢ እንዲሁም ከሠራተኞች ብሔራዊ የኢንሹራንስና ማህበራዊ ዋስትና መዋጮ መንግሥት በየዓመቱ ማግኘት የሚገባውን በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ሳያገኝ ይቀራል። ይህ ገንዘብ ለማህበራዊ ዋስትና ጥቅሞች የሚውል ነበር።

በጥቁር መሥራት ህገ-ወጥና ሥነ ምግባር የጐደለው ተግባር ከመሆኑ በተጨማሪ ሠራተኛው ላይ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊና ሌሎች ጉዳቶች ያስከትላል። ለምሳሌ፡-

  • ህመም ሲያጋጥም ደሞዝ አይኖርም
  • የእረፍት ጊዜ ክፍያ የለም
  • የጡረታ አበል ነጥብ አይኖርም
  • የሥራ-አጥነት አበል የማግኘት መብት አይኖርም
  • በሥራ ላይ ለሚያጋጥም አደጋ የሚከፈል ኢንሹራንስ አይኖርም
  • ከባንክ ብድር የማግኘት እድል አይኖርም
  • የሥራ ቅጥር ውል አይኖርም ፣ የድጋፍ ደብዳቤ ከዚያም የሥራ ልምድ ማስረጃ አይሰጥም። ሠራተኛው አዲስ ሥራ ለማግኘት ይቸገራል።

መረጃ

በጥቁር ወይም በህገ ወጥ መስራት ስነ ምግባር የጎደለዉና ህገ ወጥ ሥራም ነው።

በጥቁር መስራት ማለት ያለኮንትራትና ቀረጥ ሳይከፍሉ መስራት ማለት ነው። የሥራ ቀጣሪዉም የቀጣሪነት ክፍያና የሥራ ቀጣሪዎች ለዋስትና ቢሮ የሚከፍለትን ክፍያ አይከፍልም።