ትምህርትና የሙያ ማረጋገጫ

የትምህርት ዘዴ በኖርዌይ

የኖርዌይ የትምህርት ሥርዓት ገፅታ የሚከተለውን ይመስላል፡
Utdanningssystemet i Norge

መረጃ

የመማር ግዴታ

  • በኖርዌይ ህፃናትና ልጆች የመማር ግዳጅ አለባቸው። ይህም ማለት ሁሉም በኖርዌይ የሚኖሩ ልጆች እስከ አስር ዓመት የአንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የማግኘት መብት አላቸው።
  • ልጆች ስድስት ዓመት በሞሉበት ዓመት ዉስጥ ትምህርት ቤት ይገባሉ።
  • ሁሉም ወጣቶችና ብዙ አዋቂዎች የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የማግኘት መብት አላቸው።
  • የመንግስት ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች በነጻ ያስተምራሉ።
  • መዋለ ህፃናት ግዳጅ አይደለም፣ ነገር ግን አብዛኛቹ ልጆች ከአንድ ዓመት እስከ ሁለት ዓመት ሲሆናቸው መዋለ ህጻናት ይገባሉ።