ትምህርትና የሙያ ማረጋገጫ

መዋዕለ ህፃናት የስነ ትምህርት መርሀ ግብር ነው።

Barn og voksen i barnehage

በመዋዕለ ህፃናት ልጆች በርካታ ነገሮችን ይማራሉ፡-

  • ከሌሎች ልጆች ጋር አብሮ መሆንን ይለምዳሉ
  • ለሌሎች ማሰብን ይማራሉ።
  • ራሳቸውን ይችላሉ።
  • ብዙ እውነታዎችን ይማራሉ።
  • ትምህርት ለመጀመር የተሻለ ዝግጅት ይኖራቸዋል።

የመዋዕለ ህፃናት ሠራተኞች ህፃናት ምን መማር እንዳለባቸው ጊዜ ወስደዉ በደንብ ያቅዳሉ። እነዚህን ዕቅዶች ሲያዘጋጁ የመዋዕለ-ህፃናት ድንጋጌንና ሌሎች በባለሥልጣናት የተቀመጡ ደንቦችን መሠረት ማድረግ ያስፈልጋል። ወላጆች በመዋዕለ-ህፃናት የሚደረጉ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ዓላማዎች በተመለከተና ልጆቻቸው በየትኛው እንደሚሳተፉ መረጃ ይሰጣቸዋል።

Utelek i barnehagen
ወላጆች መዋዕለ ህፃናቱ በሚጠራው የወላጆች ስብሰባ እንዲሳተፉ እና እንዲሁም የወላጅ እና የመምህር ውይይት እንዲያደርጉ ይጋበዛሉ። በወላጆች ስብሰባ ላይ ወላጆች እርስ በርስ በመተዋወቅ ስለልጆች አስተዳደግ የሚያጋጥማቸውን ችግሮች ይወያያሉ። ኖርዌይኛ ቋንቋ መናገር የማይችሉ ወላጆች አስተርጓሚ የማግኘት መብት አላቸው።

የመዋዕለ ህፃናት ክፍያ

ኖርዌይ ውስጥ ለመዋዕለ ህፃናት የሚከፈለውን ዓመታዊ የክፍያ ጣሪያ የሚወስነው የተወካዮች ምክር ቤት ነዉ። ማንም ወላጅ በህግ ከተቀመጠው የክፍያ ጣሪያ በላይ ለመንግሥትም ይሁን ለግል መዋዕለ ህፃናት መክፈል የለበትም። ነገር ግን ለምግብ፣ ለትምህርታዊ ጉዞና ለመሳሰሉት ተጨማሪ ክፍያ ሊኖር ይችላል። ለዝርዝር መረጃ፡-
makspris barnehage

ህፃናትን በመዋዕለ ህፃናት ለማስተማር የሚከፈለው የገንዘብ መጠን እንደየወረዳዉ (ኮሚዩነ) ይለያያል። በአንዳንድ ወረዳዎች ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ወላጆች አነስተኛ ክፍያ ለመክፈል ማመልከት የሚችሉ ሲሆን ሌሎች ወረዳዎች ደግሞ ገቢን ከግምት ውስጥ ሳያስገቡ ሁሉንም ሰዎች ተመሳሳይ ክፍያ ያስከፍላሉ። ከአንድ በላይ ልጆች መዋዕለ ህፃናት ለሚያስተምሩ ወላጆች አንዳንድ ወረዳዎች የዋጋ ቅናሽ የሚያደርጉ ሲሆን ሌሎች ደግሞ ሁሉንም ተመሳሳይ ክፍያ ያስከፍላሉ።

 

መረጃ

መዋለ ህፃናት

መዋለ ህፃናት ግዳጅ አይደለም፣ ነገር ግን በኖርዌይ ውስጥ በአብዛኛዉ ልጆች ትምህርት ቤት ከመጀመራቸዉ አስቀድመዉ መዋለ ህፃናት ይገባሉ። ብቻ ነበር።
መዋለ ህፃናት የመዋለ ህፃናት ህጎችን መከተል አለባቸው። ከዚህ የተነሳ የመዋለ ህፃናት ሰራተኞችም ለልጆች የእንቅስቃሴዎች ዕቅድ ስያዘጋጁ ይህንኑ ህግ መከተል አለባቸው።
ልጆችን ወደ መዋለ ህፃናት መላክ በነፃ አይደለም። ቤተሰብ የተጠቃሚ ድርሻን በየወሩ የሚከፍል ሲሆን ቀሪውን ወጪ መንግስት ይሸፍናል።