የትምህርት ቤት መሰረታዊ ውጤቶች
እኩልነት እና የእኩል ክቡርነት እና ግለሰቦች የራሳቸውን ምርጫ የማድረግ ነፃነት የኖርዌይ ህብረተሰብ መሠረታዊ እሴቶች ናቸው። እነዚህ እሴቶች በትምህርት ውስጥም አስፈላጊ ናቸዉ። በትምህርት ቤት የሚሰጡ ትምህርቶችና የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ሁሉም ሰዎች እኩል ዋጋ እንዳላቸው ተማሪዎቻቸዉን ማስተማር አለባቸዉ። በተጨማሪም ተማሪዎች በዕለት ተዕለት የትምህርት ቤት ህይወታቸው ላይ ተፅዕኖ መፍጠር የሚችሉበትን ዕድል መጠቀምና ለትምህርታቸው ኃላፊነት መውሰድን ከልጅነታቸው ጀምሮ መማር አለባቸው። ትምህርት ቤቶች በበኩላቸው የእያንዳንዱን ተማሪ ደረጃ የሚመጥን ትምህርትና ሥልጠና የመስጠት ኃላፊነት አለባቸው።
የትምህርት ቤት ግብ ጥሩ ማህበራዊና ትምህርት ክህሎቶች ያሉት ራሱን ችሎ የሚያስብ ተማሪ ማፍራት ነው።
በዘመናዊ ዲሞክራሲ ዉስጥ ዜጐች ዕውቀት እና ነፃ አስተሳበብ እንዲኖራቸው ከማስፈለጉ በተጨማሪ በሥራ መስክና በማህበራዊ ህይወት በንቃት መሳተፍ ይጠበቅባቸዋል። ትምህርት ቤቱ ተማሪዎች ጥሩ የሆነ ጠቅላላ ዕውቀት እንዲኖራቸው ያደርጋል። ይህ ማለት ተማሪዎች ስለ ብዙ የተለያዩ አርእስተ ጉዳዮች ይማራሉ። ቋንቋ፣ ሒሳብ እና ስለህብረተሰብና ስለአካባቢያቸው ይማራሉ።
ትምህርት ቤት ለልጆች ጥሩ ጠቅላላ ዕውቀት ከማስጨበጥ በተጨማሪ ሌሎች በርካታ ኃላፊነቶች አሉበት። ለምሳሌ ልጆችን የሚከተሉትን ነገሮች ማስተማር ያስፈልጋል፡-
- መረጃ መፈለግና ያገኙትን መረጃ በጥልቀት ማጤንና መመርመር
- መረጃን በመጠቀም እና የግል ግምጋሜን በመውሰድ የራሳቸውን ሃሳብ እንዲያመነጩ ማድረግ
- ለሃሳባቸው መከራከር መቻልን
በትምህርት ቤት የሚሰጥ ትምህርት ዓላማ
(የትምህርት አዋጅ)
- ትምህርት ቤቶች እና ተለማማጅ አስተማሪ ድርጅቶች ከወላጆች ጋር በመተባበር ለዓለምና ለወደፊት ተስፋ በሮችን ክፍት ማድረግ እና እንዲሁም ታሪካዊና ባህላዊ መሠረትና ግንዛቤን በተማሪዎች ውስጥ ማስረፅ ይኖርባቸዋል።
- በመሠረታዊ የክርስትና እሴቶች እንዲሁም በሰብዓዊ ልምዶችና ቅርሶች ላይ በመመርኮዝ ለምሳሌ ለሰው ልጅ ክብርና ለተፈጥሮ ዋጋ መስጠትን፣ የአስተሳሰብ ነፃነትን፣ ሰብዓዊነትን፣ ይቅር ባይነትን፣ የእኩል ክቡርነት እና አንድነትን እንዲሁም በሰብዓዊ መብቶቹ ላይ የሰፈሩ በተለያዩ ሃይማኖቶችና ርእዮተ አለም አስተሳስቦች ላይ የሚንጸባረቁ እሴቶችን ይበልጥ ማጐልበት ይኖርበታል።
- በብሔራዊ የባህል ቅርሶችና ከሌሎች ጋር በምንጋራቸው ዓለም አቀፍ ባህላዊ ልማዶች ላይ ያለንን ዕውቀትና ግንዛቤ እንዲሰፋ አስተዋጽዖ ማድረግ ይኖርበታል።
- የባህል ብዝሃነትን ግንዛቤ ማስጨበጥ እና የእያንዳንዱን ሰው እምነት ማክበር ይኖርበታል። ዲሞክራሲን፣ እኩልነትንና ሳይንሳዊ አስተሳሰብን ማስፋፋት ይኖርበታል።
- ተማሪዎች እና ተለማማጅ ሰራተኞች