ከቤት ጋር ያለ ግንኙነት
ወላጆች ልጆቻቸውን የማሳደግ ኃላፊነት አለባቸው። ትምህርት ቤቱ ከወላጆች ጋር ተባብሮ መስራትና ላለባቸው ኃላፊነት ድጋፍ ማድረግ ይሻል። ልጆች በተቻለ መጠን ከትምህርት ቤት ጥሩ ትምህርት ማግኘት እንዲችሉ የወላጆችና የትምህርት ቤቶች ተባብሮ መሥራት አስፈላጊ ነው።
ተማሪዎች፣ ወላጆችና መምህራን እርስ በርስ ውይይት ማድረግ አስፈላጊ ነው። ስለ ልጆቹ የትምህርት እድገትና ደህንነት ዙሪያ መወያየት ያስፈልጋል። እንደዚህ ዓይነት ውይይቶች በየዓመቱ ቢያንስ ሁለት ጊዜ መደረግ አለባቸው።
ከትምህርት ቤት የሚላኩላቸውን ሁሉንም የፅሑፍ መልዕክቶች ወላጆች ማንበብ እና መከታተል አስፈላጊ ነው። ብዙ ልጆች የቤት ሥራና የጥናት መርሃ ግብር ከትምህርት ቤት ይሰጣቸዋል። እነዚህ መርሃ ግብሮች ተማሪዎቹ በየትምህርት ዓይነቶቹ ክፍል ውስጥ ምን እየተማሩ እንደሆነ ያሳያሉ። በተጨማሪም ለወላጆች ወይም ለሞግዚቶቻቸው የሚያስፈልጉ ጠቃሚ መረጃዎችን ይይዛሉ። ወላጆች ጥያቄዎች ካሏቸው መምህራንን ወይም ሌሎች የትምህርት ቤት ሠራተኞችን ማግኘት ይችላሉ።
ወላጆች ከመምህራንና ከሌሎች ወላጆች ጋር ተሰባስቦ መገናኘት የተለመደ ነዉ። በልጆቻችቸው ክፍል ስላለው የመማር ሁኔታ እና እንዲሁም ስለ እቅዶችና መርሃ ግብሮች ይወያያሉ። በየዓመቱ ቢያንስ ሁለት መሰባሰብ ይኖርባቸዋል። በእነዚህ ስብሰባዎች ላይ ተገኝቶ ከሌሎች ወላጆች ጋር መተዋወቅ መልካም ነው።