ትምህርትና የሙያ ማረጋገጫ

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት

ስለ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ጥቂት እውነታዎች

  • ኖርዌይ ውስጥ የመጀመሪያ መለስተኛና ሁለተኛ ደረጃ (ወይም ተመጣጣኙን) ያጠናቀቁ ተማሪዎች ለሦስት ዓመታት የሚሰጠውን የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የመማር መብት አላቸው።
  • አንድ ወጣት ዕድሜው 24 በሞላበት ዓመተ ምህረት ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርትን ማጠናቀቅ ይኖርበታል።
  • የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ክፍያን የሚሸፍነው የዞን ጽ/ቤቱ ሲሆን በዚህ ደረጃ የመማር መብት ላላቸዉ ሁሉ ትምህርቱን እንዲያገኙ የማስቻል ኃላፊነት አለበት።
  • የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መሰናዶ ትምህርትና የሙያ ትምህርት መርሀ ግብሮች አሏቸው። የሙያ ትምህርት የሚባሉት፡-

Elektriker Rørlegger Tømrer

መረጃ

የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

ወጣቶች ወደ 16 ዓመት ዕድሜ ሲሆናቸው የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቅቃሉ። ለዚህ ዓይነት ወጣቶቸ ብዙ ሥራ የለም። ስለዚህ ብዙዎቹ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን መቀጠል ይመርጣሉ።

ከመንግስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በተጨማሪ የግል ትምህርት ቤቶችም አሉ። በግል ትምህርት ቤት ቤተሰብ ለትምህርት ቤት ገንዘብ ይከፍላል። በርግጥ የተጠቃሚን ድርሻ ብቻ ነው የሚከፍሉት፣ ቀሪውን መንግስት ይከፍላል።

በብዙ ሙያዎች በዛሬው ጊዜ የሁለተኛ ከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ያስፍልጋል። ዋስትና ላለው ህብረተብም የብዙዎች መማር ጠቀሜታ አለው። በዚህ ዓይነት መዋዕል ማካበትና አዲስ ሥራን መፍጠር ይቻላል። ያለ ከፍተኛ ትምህርት የህብረተሰቡን ዋስትና ማቆየትና የዋስትና ድጋፎችን መቀጠል አይቻልም።

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት በነፃ ነዉ።

ተማሪዎች የመማሪያ መፅሃፍቶችን ከትምህርት ቤት የሚዋሱ ሲሆን መጻፍያና የመሳሰሉትን ራሳቸዉ መግዛት አለባቸዉ።