ትምህርትና የሙያ ማረጋገጫ

ከፍተኛ ትምህርት

På forelesning
ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ያጠናቀቁ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ገብተው መማር ይችላሉ።

አብዛኛዎቹ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች የመንግሥት ሲሆን ትምህርቱ የሚሰጠው በነፃ ነዉ። የትምህርት ክፍያውን የሚሸፈነው መንግሥት ነው። ይሁን እንጂ ተማሪዎች በየሴሚስቴሩ አነስተኛ የመመዝገቢያ ክፍያ ይከፍላሉ። እንደዚሁም ተማሪዎች የተጠቃሚ የክፍያ ድርሻ እየከፈሉ የሚማሩባቸው የግል ኮሌጆችም አሉ።

የመንግሥት ትምህርት ቤቶችና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ወጪ የሚሸፈነው በመንግሥት ስለሆነ ትምህርት ለሁሉም የሚሰጠው በነፃ ነው። ነገር ግን ተማሪዎች በመንግሥትም ሆነ በግል ትምህርት ቤቶች የራሳቸውን የመማሪያ ግብአቶች፣ መፅሐፎችና መሠረታዊ ቁሳቁሶችን ማሟላት ይኖርባቸዋል።

ምንም እንኳን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርት በነፃ ቢሆንም አብዛኛዎቹ ተማሪዎች ለሌሎች ወጪዎች መሸፈኛ የሚሆን ገንዘብ ያስፈልጋቸዋል። በመሆኑም በርካታ ተማሪዎች ከኖርዌይ የትምህርት ብድርና ድጎማ ሰጪ ጽ/ቤት (ሎነካሳ) ገንዘብ በመበደር ለቤት ኪራይ፣ ለምግብና ለሌሎች አስፈላጊ ነገሮች ያውላሉ። በዚህ መንገድ ከፍተኛ ትምህርት የመማር ፍላጐት ያላቸው ሰዎች የቤተሰቦቻቸው የገንዘብ አቅም ሳይገታቸው ራሳቸውን ችለው መማር ይችላሉ። ብዙ ተማሪዎች ደግሞ ከትምህርታቸው ጎን ለጎን የትርፍ ሰዓት ሥራ በመሥራት የኑሮ ወጪያቸውን ይሸፍናሉ።

እኩል ዋጋ ያለው የትምህርት አቅርቦት

በዘመናዊ ዓለም ያለው ህብረተሰብ የተመሰረተዉ ከፍተኛ ደረጃ ባለው የሥራ ቅጥር፣ በቴክኖሎጂ፣ በምርትና በፈጠራ ላይ ነው። በመሆኑም ኖርዌይ በከፍተኛ ደረጃ የተማረ ህዝብ ትፈልጋለች። የኖርዌይ መንግሥት ሌሎች ነገሮችን ከማድረግ በተጨማሪ ለሁሉም ሰዎች እኩል ዋጋ የሚሰጠው የትምህርት ዕድል በማመቻቸት ትምህርትን ያስፋፋል።

ኖርዌይ ውስጥ 30 በመቶ የሚሆኑ አዋቂዎች የከፍተኛ ትምህርት ዲግሪ አላቸው። በርካታ ወጣቶች ከፍተኛ ትምህርት እየከታተሉ በመሆኑ የኖርዌይ ህዝብ የትምህርት ደረጃ እያደገ ነው። በአሁኑ ወቅት 60 በመቶ በላይ የሚሆኑት ተማሪዎች ሴቶች ሲሆኑ፣ በአጠቃላይ ሴቶች ከወንዶች ትንሽ ከፍ ያለ የትምህርት ደረጃ አላቸው።

የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መልቀቅያ ፈተና ያለፈ ማንኛዉም ተማሪ ኮሌጅ ወይም ዩኒቨርሲቲ ለመግባት ማመልከት ይችላል።

የኖርዌይ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች ቅበላ አገልግሎት (ሳሞርድና ኦፕታክ) የኮሌጆችና የዩኒቨርሲቲዎች ምደባን ያስተዳድራል።

መረጃ

የመንግስት የትምህርት ብድር

የትምህርት ብድር ድርጅት በኖርዌይ ለሚማሩት ለተማሪዎች በዉጪ ለሚማሩት የኖርዊጂያን ተማሪዎች ድጋፍና ብድር ይሰጣል።

የትምህርት ብድር ድርጅት ለሚከተሉት ለዉጥ ይረዳል።

  • ይህም ሁሉም ሰው በአከባቢ፣ በእድሜ፣ በጾታና በኢኮኖሚ ሳይለይ በእኩልነት ትምህርት እንድያገኙ ይረዳል።
  • የትምህርት ሂደቱ ስኬታማ እንዲሆን ትምህርቱ በአጥጋቢ የሥራ ሁኔታ መካሄድ አለበት።
  • ማህበረሰቡ የተማረ የሥራ ኃይል እንዲያገኝ ዋስትና መስጠት።

ለአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ትምህርት አዋቂዎችም ከትምህርት ብድር ድርጅት ብድርና ድጋፍ ማግኘት ይችላል።