ትምህርትና የሙያ ማረጋገጫ

አዋቂዎችና ትምህርት

Voksen student Foto fra et norskkurs

የህብረተሰብ ለውጥ ዘወትር ይቀጥላል። በየጊዜው አዳዲስ ቴክኖጂዎች ስለሚፈጠሩ በሥራዉ ዓለም ላይ ተፅዕኖ አላቸው። ስለዚህ ሠራተኞች ራሳቸውን ከጊዜው ጋር ማስተዋወቅና አዳዲስ ክህሎቶችን መማር አለባቸዉ።

አዋቂዎች ሙሉ በሙሉ አዲስ ትምህርት ሊማሩ፣ ከዚህ በፊት የተማሩት ላይ ሊጨምሩ ወይም የሥራዉ ዓለም አሁን የሚፈልገዉን መስፈርት ለማሟላት የተወሰኑ የትምህርት ዓይነቶችን ሊወስዱ ይችላሉ።

ብዙዎች የተለያዩ ኮርሶች ለአዋቂዎች ያዘጋጃሉ። ለምሳሌ የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያ ኮርሶች፣ የቋንቋ ኮርሶች እና የብቃት ማረጋገጫ ኮርሶች ተጠቃሽ ናቸው። አብዛኛውን ጊዜ ለእነዚህ ኮርሶች የሚከፈለውን ወጪ በከፊል መንግሥት ይሸፍናል።

ወረዳዉ (ኮሚዩነ) የመጀመሪያ መለስተኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የማቅረብ ኃላፊነት ያለበት ሲሆን፣ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ደግሞ የዞኑ ኃላፊነት ነው። የመጀመሪያ መለስተኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እና የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የመከታተል መበት ያላቸው አዋቂዎች ትምህርቱን በነፃ ይማራሉ። ለአዋቂዎች የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የሚሰጡ ብዙ የግል ትምህርት ቤቶችም አሉ።

ሥራ ፈላጊዎች በኖርዌይ ሠራተኛና ማህበራዊ ዋስትና አገልግሎት (ናቭ) በኩል የተለያዩ ኮርሶችን የመከታተል ዕድል ሊያገኙ ይችላሉ። የኮርሶቹ ዓላማ ተሳታፊዎችን ለሥራዎች ብቁ ማድረግ ነው። ናቭ የሥልጠናውን ወጪ ከመሸፈን ባሻገር አብዛኛውን ጊዜ ለተሳታፊዎች የትምህርት ክፍያ ይከፍላል።

መረጃ

የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ለማግኘት አዋቂዎች ያላቸዉ መብት

የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት የሚፈልጉ አዋቂዎች የማግኘት መብት አላቸው። ትምህርቱም ያለ ክፍያ ነዉ። ወረዳዉ በዚህ ጉዳይ ላይ የበለጠ መረጃ መስጠት ይችላል።

አዋቂዎች ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ያላቸው መብት

የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርትን ያጠናቀቁ ነገር ግን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ያላገኙ አዋቂዎች የሁለተኛ ደረጃ ትምህርትን የማግኘት መብት አላቸዉ። ለዚህ ኃላፊነት ያለዉ የዞን (ፍልክስ ኮሙነ) አስተዳደር ነዉ።

የዉጪ አገር ትምህርቶች እውቅና ስለመስጠት

በዉጪ አገር የተማሩት ሙያ ካለና ለዚህ የመረጃ ወረቀት ከሌለዎ በሙያ ሰርቶ በማሳየት ማስመስከር ይችላሉ። ሙያ በስራ ማሳየት በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ያለውን ችሎታ ማሳያ ዘዴ ነዉ። ይህም ማለት ሰው ትምህርት ቤት ሳይሄድ ዕውቀቱን ተምሮትም ሊሆን ይችላል። ለበለጠ መረጃ የ NOKUT ይመልከቱ።