ታሪካዊ እድገት
ኖርዌይ ረጅም የመማር-ማስተማር ታሪክ አላት። በ1700ዎቹ የሃገሪቱ የኢኮኖሚ ሁኔታ እጅግ በጣም ደካማ ነበር። ይሁን እንጂ የትምህርት አስፈላጊነት ስለታመነበት ሁሉም ልጆች ትምህርት ቤት ገብተው እንዲማሩና መንግሥት የትምህርት ክፍያን እንዲሸፍን ተወሰነ።
- ከ18ኛው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያ አጋማሽ ጀምሮ ለሁሉም ወንድና ሴት ልጆች ትምህርትን በነፃ መማር ግዴታ ሆነ። ይህም እያንዳንዱ ሰው የማንበብ ችሎታ ኖሮት መፅሐፍ ቅዱስን በራሱ ማጥናት እንዲችል የታሰበ ነበር። በተጨማሪም ሁሉም ልጆች ስለክርስትና ትምህርት ማግኘት ነበረባቸው።
- በዚያን ጊዜ በየቀኑ ወደ ትምህርት ቤት መሄድ የተለመደ አልነበረም። ብዙ ልጆች ወደ ትምህርት ቤት የሚሄዱት በሁለት ቀን አንዴ ወይም በዓመት ውስጥ ለጥቂት ሣምንታት ብቻ ነበር።
- ትምህርት ቤቶች ቀስ በቀስ ተጨማሪ የትምህርት ዓይነቶች መስጠት ጀመሩ። ለምሳሌ መፃፍ፣ ሂሳብ እና ሙዚቃ በ1800ዎቹ መጀመሪያ ላይ የግድ የሚወሰዱ የትምህርት ዓይነቶች ነበሩ።
- በ1936 ሁሉም ልጆች ቢያንስ ለሰባት ዓመታት ትምህርት ቤት ገብተው መማር እንዳለባቸው ተወሰነ። ከ1997 ጀምሮ ደግሞ የግዴታ ትምህርት አሥር ዓመታት ሆኗል።
- በተለያዩ ትምህርት ቤቶች አገልግሎት ላይ የሚውሉ ሥርዓተ ትምህርቶች (ካሪኩለሞች) በተወካዮች ምክር ቤት ይፀድቃሉ። በመሆኑም በየትኛውም የሃገሪቱ ክፍል የሚገኙ ትምህርት ቤቶች አንድ ዓይነት ትምህርት ያስተምራሉ ማለት ነው።