ስደተኞች ሊጠቀሙባቸው የሚችሉ የተለያዩ አገልግሎቶች

ስደተኞች ሊጠቀሙባቸው የሚችሉ የተለያዩ አገልግሎቶች

ወደ ኖርዌይ የመጣ አዲስ ሰው ከተለያዩ ብዙ መስሪያ ቤቶች እና መስኮች ጋር ግንኙነት ያደርጋሉ። ይህም ለምሳሌ እንደ መዘጋጃ ቤት፣ የመዋለ ህፃናት፣ ሀኪም ቤቶች፣ የአገር ዉስጥ ገቢ (ቀረጥ) ባለስልጣናት እና የስራና ድጋፍ ዋስትና (NAV) የመሳሰሉትን ይመለከታል። እዚህ ጋር የተወሰኑትን በቀረቤታ እንመለከታለን። እነዚህ የተለያዩ ቢሮዎች ምን እንደሚሰሩና እንዴት ማግኘት እንደሚቻል ማወቅ ጠቃሚ ነው።ባሁን ጊዜ ብዙ ጉዳዮች መንግስታዊ እና ሌሎች ቢሮዎች ለማመልከት በኢንተርኔት ሆኗል። ብዙ ቅፆችን ከኢንተርኔት መውሰድ የሚቻል እና ብዙ መረጃዎችንም ከተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ድህረገፆች ማግኘት ይቻላል። ሁሉም ወረዳዎች በየድህረገፆቻቸዉ መረጃ ም ለነዋሪዎች ይሰጣሉ። የአገር ዉስጥ ገቢ (ቀረጥ) ባለስልጣናት የአገር ዉስጥ ገቢ ባለስልጣናት ቀረጦችና ክፍያዎች ስለመከፈላቸው ሃላፊነት አላቸው። ከአገር ዉስጥ ገቢ ባለስልጣናት ቀረጥ ካርድ መግኘት ይችላሉ። ስራ ለመስራት ወይም ቀረጥ ሊከፍሉበት የሚገባ ገቢ ካገኙ ይህ የቀረጥ ካርድ ያስፈልጎታል። ብዛት ያላቸው የአገር ዉስጥ ገቢ ባለስልጣናት አገልግሎቶች በኢንተርኔት ማከናወን ይቻላል። ማዘጋጃ ቤት (ፎልኬ ሬጂስተር)t ማዘጋጃ ቤት የአገር ዉስጥ ገቢ ባለስልጣናት አንዱ አካል ነው። ይህ በኖርዌይ አገር የሚኖሩ እና ኖረው የነበሩ ሰዎች መንግሰታዊ መመዝገብያ ነው። ሁሉም አድራሻ የሚቀይሩ አድራሻ መቀየራቸውን በ8 ቀን ውስጥ ለመዘጋጃ ቤት ማሳወቅ ይኖረባቸዋል። ይህንንም በኢንተርኔት ማድረግ ይችላሉ። ማዘጋጃ ቤት ስም መለወጥ፣ የትውልድ ቁጥሮችን እና ዲ ቁጥሮችን (D-nummer) የማደል ሃላፊነት አለበት። አንድ ሰው ማግባት ቢፈልግ መዘጋጃ ቤት ማሳወቅ ይኖርበታል። የስራና ድጋፍ ዋስትና ቢሮ የስራና ድጋፍ ዋስትና ቢሮ (NAV) ብዙ የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚሰጥ አንድ የመንግስት ቢሮ ነው። የስራና ድጋፍ ዋስትና ቢሮ ካሉት የተወሰኑት ሃላፊነቶች መካከል፤

  • የልጆች የድጋፍ ክፍያ
  • መዋለ ህጻናት ለማይሄዱ ልጆች ክፍያ
  • የህመም ጊዜ ክፍያ
  • የስራ አጥነት ክፍያ
  • ለመስራት ብቁ ላልሆኑ የሚከፈል ጡረታ
  • ጡረታ

የስራና ድጋፍ ዋስትና ቢሮ በተጨማሪም ስራ ለሌላቸውም አገልግሎቶች ይሰጣል። ብዙዎች የስራና ድጋፍ ዋስትና ቢሮ እየከፈለላቸው ኮርስ(ትምህርት) ይማራሉ፣ ይህም አላማው በኮረሶቹ ላይ የተካፈሉት ስራ ማግኘት እንዲችሉ ነው። አስተርጓሚ የማግኘት መብት አንድ ስደተኛ በቂ የኖርዊጂያን ቋንቋ ከመማሩ በፊት አስተርጓሚ መጠቀም አስፈላጊ ሊሆን ይችላል። የመንግስት ሰራተኞች ለምሳሌ እንደ የስራና ድጋፍ ዋስትና ቢሮ ፣ ፖሊስ እና የህክምና ጣቢያዎች መረጃዎች እና መመሪያዎች ሰዎች እንዲረዱት የማድረግ ግዴታ አለባቸው። ስለዚህም አስተርጓሚ ማግኘት የስደተኞች መብት ሲሆን ወጪውንም መንግስት ይሸፍናል።