የኖርዌይ የሥራ ገበያ
ፊልሙን ይመልከቱ
የኖርዌይ የሥራ ገበያ
ከ 150 ዓመታት በፊት፡ በኖርዌይ፡ ግብርና፡ ደን እና ዓሳ ማጥመድ በጣም አስፈላጊ ኢንዱስትሪዎች ነበሩ። ከዚያ ወዲህ ግን ብዙ ለውጦች ተከስቷል። በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ ፋብሪካዎች ስለ ተቋቋሙ፡ ብዙ ሰዎች ለመሥራት ወደነኚህ መንደሮችና ከተሞችን ተዛወሩ። በ20ኛው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያ አጋማሽ፡ በኢንዱስትሪ ዘርፍ ብዙ አዳዲስ ሥራዎች ተፈጥሯዋል። በተመሳሳይ ጊዜ ደግሞ፡ ብዙ ኖርዌጂያውያን ወደ አሜሪካ በመሔድ እዚያ ሰፈሩ።
በ1950፡ ከ20% በላይ ሕዝብ፡ በግብርና መስክ ተሰማርቶ ይሠራ ነበር። በኣሁኑ ግዜ ግን፡ ይህን ቊጥር ከ3% በታች ወርደዋል። ቢሆንም፡ ኖርዌይ ከበፊቱ የበለጠ ምግብ ታመርታለች። ምክንያቱም፡ በአሁን ግዜ፡ የምግብ ምርትን ቀላል እና ቀልጣፋ የሚያደርጉ የእርሻ ማሺኔሪዎች ስላሉ ነው።
በ 1960 ዎቹ መገባደጃ ላይ፡ በሰሜን ባህር ውስጥ የነዳጅ ክምችት ከተገኘ በኋላ፡ የነዳጅ እና የጋዝ ምርት የኖርዌይ የኢንዱስትሪ ዘርፍ አስፈላጊ አካል ሆነ። ነዳጅ እና ጋዝ ለኖርዌይ ኢኮኖሚ በጣም አስፈላጊ ነበሩ። ምንም እንኳን የአየር ንብረት ተግዳሮቶች ወደ ‹አረንጓዴ› ሥራዎች መሸጋገር የሚያስፈልጋቸው ቢሆኑም፡ አስፈላጊ ሆነው ይቀጥላሉ።
ባለፉት 30 ዓመታት፡ በኖርዌይ ያለው የሥራ ገበያ እንደገና፡ ትልቅ ለውጦችን አሳይቷል። ከሌሎች ነገሮች በተጨማሪ፡ በኢንዱስትሪ ውስጥ የሚሠሩ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል። ዛሬ አብዛኛዎቹ ሥራዎች በአገልግሎት ሙያዎች ውስጥ ይገኛሉ። ይህ ማለት፡ በኖርዌይ ሥራ የሚፈልጉ ሰዎች፡ በሱቅ ውስጥ፡ በጤና ኣገልግሎት፡ በትምህርት ቤት ወይም በመዋዕለ ሕጻናት ዘርፎች፡ ወይም በተሳፋሪ መጓጓዣ፡ ሥራ የማግኘት ዕድሉ ጥሩ ነው። ብዙ ሰዎች ከመረጃ ቴክኖሎጂ ልማት ጋር በተያያዙ ሙያዎችም ሥራ ማግኘት ይችላሉ።
ኣብራችሁ ተወያዩ
- ሰንጠረጁ ምን ይነግረናል?
- በሚታውቋቸው አገሮች ውስጥ፡ የተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ስርጭት ምን ይመስላሉ?
- በየትኛቹ ሙያዎች ሥራ ልታገኝ ትችላለህ?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
የነዳጅ እና ጋዝ ምርት፡ ለኖርዌይ የኢንዱስትሪ ዘርፍ፡ ኣስፈላጊ የሆነው መቼ ነው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
በኖርዌይ፡ በኣሁን ግዜ፡ አብዛኛው ሥራ ምን ላይ የተመረኮሰ ነው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ከ150 ዓመታት በፊት፡ በኖርዌይ የትኞቹ ኢንዱስትሪዎች በጣም አስፈላጊ ነበሩ?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?
ትክክለኛውን ምስል ይምረጡ
በኣሁን ግዜ፡ አብዛኛዎቹ ሥራዎች በአገልግሎት ሙያዎች ውስጥ ይገኛሉ። የትኞቹ ምስሎች የአገልግሎት ሙያዎችን ያሳያሉ? ከአንድ በላይ ምስል መምረጥ ይችላሉ።