ምርጫዎች እና የፖለቲካ ፓርቲዎች
ምርጫዎች እና የፖለቲካ ፓርቲዎች
በኖርዌይ በየሁለት ዓመቱ የፖለቲካ ምርጫ ይካሄዳል። ምርጫዎቹ፡ የአጠቃላይ፡ የአውራጃ እና የኣከባቢ ኣስተዳደሮች ሆነው፡ በየተራ ይካሄዳል።
የፖለቲካ ፓርቲዎች: በፓርቲያቸው ጉባኤዎች ላይ የራሳቸውን ማኒፌስቶ ያዘጋጃሉ፡፡ በማኒፌስቶውም ውስጥ ፓርቲው በቀጣዩ አራት አመት: የትኞቹ ጉዳዮች ቅድሚያ ሊሰጣቸው እንደሚገባ በግልጽ ያስቀምጣሉ፡፡
በኖርዌይ ውስጥ ምርጫ የሚካሄደው በሚስጥር ድምጽ ነው። ይህ ማለት የትኛውን ፓርቲ እንደምንመርጥ ለሌሎች ሰዎች መንገር አያስፈልገንም ማለት ነው። በአንድ ቤተሰብ ውስጥ ያሉ ሰዎች ብዙውን ጊዜ ለተለያዩ ፓርቲዎች ይመርጣሉ። የትኛውን ፓርቲ እንደሚደግፉ ገለልተኛ አስተያየት መያዝ አስፈላጊ ነው።
የመምረጥ መብት
- በኖርወይ የመምረጥ እድሜ 18 ዓመት ነው።
- በጠቅላላ ምርጫ (ስቶቲንግ) ድምጽ ለምስጠት፡ የኖርወይ ዜጋ መሆን ኣለቦት።
- በኣውራጃ እና የኣከባቢ ኣስተዳደር ምርጫ ድምጽ ለመስጠት፡ ላለፉት ሶስት ዓመታት በኖርወይ መኖር ኣለቦት።
- የኖርዌይ ወንዶች ከ1898 ዓ.ም.፡ ጀምሮ የምርጫ ድምጽ መስጠት መብት ሲያገኙ፡ ለኖርዌይ ሴቶች የምርጫ ድምጽ መስጠት መብት የተሰጣቸው ግን በ1913 ዓ.ም. ነው።
የፖለቲካ ፓርቲዎች
በኖርዌይ ውስጥ ሃያ ሁለት የሚያህሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሉ፣ ስለዚህ በምርጫ ወቅት ብዙ አማራጮች አሉ ማለት ነው።
ትላልቆቹን ፓርቲዎች ብግምት ከ‘ሶሻሊስት’ እስከ ‘ወግ አጥባቂ’ በሚለው ሚዛን ላይ ልናስቀምጣቸው እንችላለን።
ኣብራችሁ ተወያዩ
- እናንተ በምታውቁት አገር ፖለቲካዊ ምርጫ የሚካሄደው እንዴት ነው?
- በፖለቲካዊ ምርጫ ድምጽ መስጠት ጠቃሚ እንደሆነ ታስባላችሁን ? አዎን ከሆነ ለምን? አይ ከሆም ለምን?
- በኖርዌይ ስለሚገኙ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ታውቃላችሁ?
- ስለ ፖለቲካ ፓርቲዎች መረጃ ለማግኘት እንዲሁም ለምን አላማ እንደተሰለፉ ለማወቅ ምን ማድረግ ይገባችኋል?
- የኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ማናቸው? የትኛውን የፖለቲካ ፓርቲ ይወክላሉ?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
በኖርዌይ ውስጥ ፖለቲካዊ ምርጫዎች በምን ያክል ጊዜ ይከናወናሉ?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
በኖርዌይ ውስጥ ምርጫ የሚካሄደው በሚስጥር ድምጽ መስጫ ውስጥ ነው ማለት ምን ማለት ነው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
በኖርዌይ ውስጥ ምን ያክል የፖለቲካ ፓርቲዎች አሉ?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ፡፡ ትክክል የትናው ነው? ስህተት የትኛው ነው?
ስዕሉን ተጭነው ይክፈቱ
ወግ አጥባቂ ፓርቲ የሆነው ላይ ክቡን ተጫኑት፡፡
ስዕሉን ተጭነው ይክፈቱ
የሶሻሊስት ፓርቲውን ክብ ተጫኑት፡፡