ሰብአዊ መብት

Lærerinnhold

Tips til undervisningen

Læreren må sjekke hvilket forhold deltakerne har til FN og menneskerettigheter.

Hvilke menneskerettigheter kjenner deltakerne til? Om det passer, diskuter deltakernes hjemland og menneskerettigheter.

Tips til undervisninga

Læraren må finne ut kva deltakarane veit og tenkjer om FN og menneskerettane.

Kva for menneskerettar kjenner deltakarane til? Om det passar, diskuter menneskerettar og heimlanda til deltakarane.

Læreplan

Grunnleggende ferdigheter

Digitale ferdigheter
Muntlige ferdigheter

Tverrfaglige tema

Demokrati og medborgerskap

Læreplan i samfunnskunnskap for voksne innvandrere etter integreringsloven

samtale om menneskerettigheter som ytringsfrihet og vern mot diskriminering

Kjerneelement

Demokratiforståelse og deltakelse

Læringsaktivitet

Muntlig aktivitet

ሰብአዊ መብት

Illustrasjonsfoto.
GettyImages

ሰብአዊ መብቶች ሁለንተናዊ መብቶች ናቸው። እነሱ እንደ ሰው ሁላችንም ያሉን መብቶች ናቸው - በተወሰነ የአለም ክፍል ውስጥ ስለምንኖር ወይም የአንድ ሀይማኖት ወይም ጎሳ አባል ስለሆንን አይደለም። ለዚህም ነው ሰብአዊ መብቶችን ሁለንተናዊ /ዓለም ኣቀፋዊ/ ብለን የምንጠራው።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶችን ድንጋጌ በ1948 ዓ.ም. ነበር የጸደቀው። 193ቱም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል ኣገራት ይህንን ድንጋጌ ተቀብለው የራሳቸው አድርገውታል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ድንጋጌ አብዛኛው ክፍል ከኖርዌይ ሕጎች ውስጥ ተካተዋል።

ከሌሎች ነገሮች በተጨማሪ የሰብአዊ መብቶች መግለጫው እንዲህ ይላል፦

  • ማንኛውም ሰው እኩል ሰብአዊ ክብርና መብት ያለውና ነጻ ሆኖ ነው የተወለደው፡፡
  • ማንኛውም ሰው ከስርአተ ጾታ፣ ሃይማኖቱ፣ ዘሩ እና ፓለቲካዊ አመለካከቱና፣ ዜግነቱ ጋር ባልተገናኘ እኩል ሰብአዊ መብት አለው፡፡
  • ማንኛውም ሰው የነጻነትና ሰብአዊ ደኅንነት የማግኘት መብት አለው፡፡
  • የትኛውንም አይነት ስቃይ በሰዎች ላይ ማድረስ ክልክል ነው፡፡
  • ማንኛውም ሰው የደሕንነት ሂደት ሃላፊነት አለበት፡፡
  • ማንኛውም ሰው፡ በምስጢር በሚደረግ ምርጫ፡ በአገሩ የፖለቲካ ሁኔታ ላይ ተጽእኖ የማድረግ መብት አለው።

ኣብራችሁ ተወያዩ

  • የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች መግለጫን ያውቁታል?
  • የሰብአዊ መብቶች መግለጫ በዓለም ዙሪያ በሰዎች የኑሮ ሁኔታ ላይ ተጽእኖ አለው ብለው ያስባሉ?
  • ሁሉም የአለም ኣገራት በመግለጫው ላይ የተቀመጡትን ድንጋጌዎች ያከብራሉ?

ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አለማቀፋዊ የሰብአዊ መብት ድንጋጌን ያወጀው መች ነበር?

ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ

ሰብአዊ መብቱ ተግባራዊ የሚሆነው ለማን ነው?

ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ

የትኛው አማራጭ ነው ሰብአዊ መብት ያልሆነው?

ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ

መግለጫዎቹን ያንብቡ። ትክክል የቱ ነው? ስህተት የሆነው የቱ ነው?

ሰብአዊ መብት ዓለምአቀፋዊ ነው ብለናል፡፡
ሰብአዊ መብት አልተሟላም ብለናል፡፡
ሰብአዊ መብት ለሁሉም አንድ አይነት ነው በለናል፡፡

ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ

መግለጫዎቹን ያንብቡ፡፡ ትክክል የቱ ነው? ስህተት የቱ ነው?

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ድንጋጌን የደነገገው እ.ኤ.አ በ1948 ነው፡፡
ሁሉም ሰው እኩል ሰብአዊ መብት አለው፡፡
ድንጋጌው ሰዎችን ማሰቃየት በአንዳንድ ሁኔታዎች ሊፈቀድ ይችላል በማለት ይደነግጋል፡፡
የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ድንጋጌን የያዙት ትልልቆቹ በራሪ ወረቀቶች ከኖርዌያውያ ሕግ ጋር አብረው አይሄዱም፡፡
ድንጋጌው ምርጫ ግልጽ መሆን አለበት ድምጽ የሰጣችሁ ለማን እንደሆነ ደግሞ መናገር ይኖርባችኋል ይላል፡፡