የግዳጅ ጋብቻ
የግዳጅ ጋብቻ
ከጋብቻ ሕግ፡
- ማንኛውም 18 አመት የሞላው/ት ከዚህ ቀደም ያላገባ/ች የኖርዌይ ሕጋዊ ነዋሪ የሆነ ሰው የጋብቻ ውል መፈጸም ይችላል/ትችላለች፡፡
- ጋብቻ የሚፈጸመው በፈቃደኝነት መሆን ኣለበት። ወንዶችም ሆኑ ሴቶች፡ የሚያገቡትን ሰው በነጻነት የመምረጥ መብት አላቸው። የወንጀለኛ መቅጫ ሕጉ፡ ማንኛውም ሰው፡ በኃይል፣ ነፃነት በማሳጣት፣ በግፊት ወይም በማስፈራራት፡ አንድን ሰው ጋብቻ እንዲፈጽም ያስገደደ፡ እስከ ስድስት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ይቀጣል።የግዳጅ ጋብቻን የደገፈ፡ ወይም በዚህ ጉዳይ የተሳተፈ ሰው በተመሳሳይ ሁኔታ ይቀጣል።
- ሁለት፡ የተለያየም ወይም ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው ሰዎች ጋብቻ መፈጸም ይችላሉ፡፡
የትዳር አጋር መፈለግ
በፍቅር ላይ የተመሰረተ ትዳር፡ ተጋቢዎቹ አንደኛው ሌላኛውን በራሱ ምርጫ ፈልጎና ወስኖ የሚፈጽሙት የጋብቻ አይነት ነው።
በቤተሰብ የሚደረግ ትዳር፣ ወላጆች አሊያም የቤተሰብ አባላት ለልጆቻቸው ኣጋር የሚሆን ሰው በመፈለጉ ረገድ ወሳኛ ሚና የሚጫወቱበት የጋብቻ አይነት ነው። ልጆቻቸውም የቤተሰቦቻቸውን ምርጫ በፈቃዳቸው ተቀብለው ወደ ትዳር የሚገቡበት ሁኔታ ነው፡፡
የግዳጅ ጋብቻ: ወላጆች ለልጆቻቸው የትዳር ጓደኛ ፈልገው እንዲያገቡ ጫና ያደርጉባቸዋል:; በኖርዌይ ማንንም ሰው እንዲያገባ ማስገደድ ህገወጥ ነው። ማንም ሰው እንዲያገባ ያስገደደ ወይም የሚገፋፋ እስከ ስድስት ዓመት በሚደርስ እስራት ይቀጣል። የግዳጅ ጋብቻ በኖርዌይ ህግ ተቀባይነት የለውም። አንድ ሰው እንዲያገባ የተገደደ ወይም የሚገፋፋ ሰው ወደ ኖርዌይ ፍርድ ቤት ሄዶ ጋብቻው እንዲፈርስ ማድረግ ይችላል። ይህ ከተጋቡ በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ መደረግ አለበት.
ኣብራችሁ ተወያዩ
- በሦስቱ የተለያዩ የጋብቻ ዓይነቶች መካከል ግልጽ የሆኑ ድንበሮች አሉን?
- ሰዎች ኃይልን በተለየ መንገድ ሊገልጹ ይችላሉን?
ሚና 18 አመቷ ነው፡፡ ከቤተሰቦቿ ጋር ወደ ኖርዌይ የመጣችው በአስር አመቷ ነበር፡፡የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን ጨርሳ ትምርቷን መቀጠል እየተዘጋጀች ነው፡፡ የኢንጂነሪንግ ትምህርት ለመማር ማመልከቻ አስገብታ ምላሹን በጉጉት በመጠባበቅ ላይ ነች፡፡
ወደፊት፡ ትዳር ይዛ ልጆች ወልዳ የመኖር ፍላጎት አላት፡፡ መቼ ማግባት እንዳለባትና ማንን ማግባት እንዳለባት መወሰን ትፈልጋለች። ቢሆኖም፡ ቤተሰቦቿ ስለጋብቻ ደጋግመው ማውራት ጀምረዋል። በትውልድ ሃገራቸው የሚኖር አንድ ዘመዳቸው እንዳለ እና ይህ ሰው ደግሞ ለሚና ትክክለኛ ባል ሊሆን እንደሚችል ያወራሉ። ሚና ግን እንቅልፍ ርቋታል። የቤተሰቦቿን ምኞት እውን እንዲሆን ትመኛለች፣ ይሁን እንጂ፡ በራሷ ሕይወት ላይ መወሰን ትፈልጋለች፡፡
- ሚና ስላለችበት ሁኔታ ተወያዩ፡፡
- ወላጆቿ ሁኔታውን እንዴት ነው የሚያዩት?
- ለዚህ ቤተሰብ ከሁሉ የተሻለው መፍትሄ ምንድነው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
በኖርዌይ ውስጥ ማግባት የሚፈቀደው መቼ ነው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ጋብቻ ውስጥ መግባት የሚችለው ማነው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ለልጆቻቸው ሚስት የሚመርጡ ቤተሰቦች ከየትኛው የቤተሰብ አይነት ይመደባሉ?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ ፡፡
መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?