ሥራ ማግኘት የሚቻሉባቸው መንገዶች
ሥራ ማግኘት የሚቻሉባቸው መንገዶች
በኖርዌይ ውስጥ ሥራ ሲፈልጉ በርካታ አማራጮች አሉ፡-
- አውታረ መረብዎን መጠቀም፡
- ኢንተርነት - nav.no እንዲሁም finn.no
- ግዜያዊ ሠራተኞችን የሚቀጥሩ ጽሕፈት ቤቶች
ብዙ አሠሪዎች ማጣቀሻዎች አስፈላጊ ናቸው ብለው ያስባሉ። ከዚያ በመነሳት፡ አመልካቹ በሥራ ቦታ እንዴት እንደሆነ፡ የቀድሞ አሠሪዎችን መጠየቅ ይችላሉ። አንድ የቀድሞ አለቃ ወይም የሥራ ባልደረባ ጥሩ ማጣቀሻዎችን ሊሰጥ ይችላል።
በኖርዌይ፡ የመጀመሪያውን ሥራ ማግኘት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፡ ምክንያቱም ማጣቀሻዎች ስለጎደለህ ወይም አነስተኛ አውታረ መረብ ስላለህ። ስለዚህ፡ በሥራ ቦታ ለተወሰነ ግዜ በሥራ ላይ መሆን፣ አንዳንድ ኮርሶችን ወይም የመሳሰሉትን መከታተል ብልህነት ሊሆን ይችላል። በተግባር እና በተለያዩ ትናንሽ ሥራዎች አማካይነት፡ አውታረ መረብህን ማስፋፋት እና ማጣቀሻዎችን ማግኘት ትችላለህ።
በኖርዌይ፡ ከስልሳ እስከ ሰማንያ በመቶ የሚሆኑት ሥራዎች ማስታወቂያ አይደረግላቸውም፡ ነገር ግን፡ በኣውታረ መረብ አማካይነት ይደርጋል ይባላል። አውታረ መረብ ሲባል፡ የምናውቃቸው፡ የምንገናኛቸው እና የምንገናኝባቸው ሰዎች ሁሉ ያጠቃልላል። የእኛ አውታረ መረብ ቤተሰብ፡ ዘመዶች፡ ጓደኞች፡ የምናውቃቸው፣ የሥራ ባልደረቦች፡ ጎረቤቶች፡ መምህራን እና የጉዳይ ሠራተኞች ሊያካትት ይችላል።
ኣብራችሁ ተወያዩ
- በአገርዎ ሰዎች ሥራ ማግኘት ምን ያህል የተለመደ ነው ወይ?
- በኖርዌይ፡ ሥራ ስለሚገኙባቸው መንገዶችን ተነጋገሩ፡
- ወደ ኖርዌይ ከመምጣትዎ በፊት፡ በአውታረ መረብዎ ውስጥ እነማን ነበሩ? ኣሁንስ፡ በአውታረ መረብዎ እነማን ኣሉ?
- በኖርዌይ፡ ትልቅ አውታረ መረብ ይፈልጋሉ? እሱን ለማስፋፋት ምን ያደርጋሉ?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ማጣቀሻ ምንድነው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
አውታረ መረብ ምንድነው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
በኖርዌይ፡ ክፍት የሥራ ቦታዎችን ማስተዋወቅ የተለመደ ነውን?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ሰዎች ሥራ በሚፈልጉበት ጊዜ ብዙውን ጊዜ የትኞቹን በይነመረብ ጣቢያዎች ይፈትሻሉ?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?