የልጆች እና የወጣቶች መብቶች
የልጆች እና የወጣቶች መብቶች
የልጆች እና የወጣቶች መብቶች
በኖርዌይ የልጆች ሕግ የሚባል አለ። ተግባራዊ የሚሆነውም ከ18 አመት በታች ባሉ ልጆች ላይ ሲሆን: ወላጆች ለልጆቻቸው ማድረግ ስለሚገባቸው ነገርና: ልጆች በቤሰቦቻቸው ላይ ያላቸውን መብቶች የሚያስገነዝብ ሕግ ነው።
በልጆች ሕግ ውስጥ ያሉ ጠቃሚ ነጥቦች እነሆ፦
- አንድ ልጅ ሲወለድ ብሔራዊ ምዝገባ እንዲያውቀው ይደረጋል። የእውቅና ሂደቱም የልጁ እናት እና አባት ማን እንደሆኑና ኣብረው ይኖሩ እንደሆነም ያመለክታል።
- እንደ ሕግ ወላጆች ለልጆቻቸው ተቀዳሚውን ኃላፊነት ይወስዳሉ፡ ልጆችም በወላጆቻቸው እንክብካቤና ጥበቃ የማግኘት መብት አላቸው።
- ልጆቻቸው 18 አመት እስኪሞላቸው ድረስ፡ ወላጆች ለልጆቻቸው ምግብና ልብስ እንዲሁም የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች እንዲኖራቸው ማረጋገጥ ይገባቸዋል።
- ወላጆች ልጆቻቸውን በአግባቡ የማሳደግ ኃላፊነት እና ልጆቻቸው ለሚፈልጉት እና ለሚያስፈልጓቸው ነገሮች ትኩረት ሊሰጡ ይገባል። የልጆች መብትና ደህንነት ጥበቃ ሕግ የሚባለው አሰራር ልጆች በሚያድጉበት ጊዜ ጸብ እንዳይኖር በጥብቅ ይከለክላል።
- ወላጆች ልጆቻቸው የግዴታ የመጀመሪያ ደረጃ እና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እንዲማሩ እና አቅማቸውን እና ፍላጎታቸውን የሚያሟላ ትምህርት እንዲወስዱ ማረጋገጥ አለባቸው።
- ወላጆቻቸው ተለያይተው የሚኖሩ ቢሆን እንኳን ልጆች ወላጆቻቸውን የማግኘት መብት አላቸው።
- ልጆች በራሳቸው መወሰን በማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ ወላጆች ልጆቻቸውን ወክለው የመወሰን መብትና ግዴታ አለባቸው። አንድ ልጅ በእድሜ እያደገ በሚሄድበት ወቅትም ወላጆች ለልጃቸው አመለካከት ስፍራ መስጠት ይኖርባቸዋል። ሰባት አመት የሞላቸው ልጆች ሃሳባቸውን በወላጆቻቸው ፊት የመግለጽና ልጆቹን በሚመለከት የግል ጉዳይ ላይ ውሳኔ የማድረግ መብት አላቸው። የልጆች ሕግ፡ አንድ ልጅ 12 አመት በሚሞላው ጊዜ፡ የልጁ ሃሳብ ኣመዛኝ ክብደት እንዲኖረው ይላል።
- 15 አመት የሞላቸው ልጆች ከትምህርታቸው እና ከሚቀላቀሉት ወይንም ከሚለቁትን ድርጅት ጋር በተያያዘ ውሳኔ የማድረግ መብት አላቸው።
- በኖርዌይ የአቅመ አዳም እድሜ 18 አመት ነው። ይህ ማለት ሕጋዊ ስምምነቶችን የማድረግና የራሳቸውን ገንዘብ የማስተዳደር መብታቸውን ይጠቀማሉ።ወላጆች ለልጁ ተጠያቂ አይደሉም።
ኣብራችሁ ተወያዩ
- ስለ ፎቶዎች ተነጋገሩ። ከልጆች መብትና ደህንነት ጥበቃ ሕግ ጋር ምን ግንኙነት አላቸው?
- ልጆችን በተለየ መንገድ የሚጠብቅ እንቅስቃሴ ያላቸው ሌሎች የምታውቋቸው አገራት ይኖሩ ይሆን?
- የልጆች ጥበቃ ሕግ ለወላጆች ምን ማለት ነው?
- ልጆች ጥሩ ሕይወት ይኖራቸው ዘንድ ምን ያስፈልጋቸዋል?
- የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምርት ምርጫቸውን በተመለከተ የ15 አመት ልጆች ያሏቸው ወላጆች ምን አይነት ሚና ይኖራቸዋል?
- የልጆችን መብት ከሚያስጠብቀው ሕግ ውስጥ የትኛው ሕግ ይበልጥ ጠቃሚ ይመስላችኋል?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
በልጆች (የጥበቃ) ሕግ የሚሸፈነው ማነው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
የልጆች (የጥበቃ) ሕግ አገልግሎት ልጆችን በማሳደግ ጊዜ ስለሚፈጠር ግጭት ምን ይላል?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ልጆች የመጀመሪያ ደረጃ እና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መግባታቸውን የማረጋገጡ ሃላፊነት የማነው ?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?