ጋብቻ እና ቤተሰብ
ፊልሙን ይመልከቱ
ጋብቻ እና ቤተሰብ
ጋብቻ እና ቤተሰብ
- አብረው ከሚኖሩ ጥንዶች ሰላሳ ከመቶ የሚሆኑት ሳይጋቡ አብረው የሚኖሩ ናቸው። ሰባ ከመቶ የሚሆኑት ደግሞ ተጋብተው የሚኖሩ ናቸው።
- ለወንዶችም ሆነ ለሴቶችም፡ የመጀመሪያ የጋብቻ አማካይ ዕድሜ፡ በ30 እና 40 ዓመት መካከል ነው።
- በየዓመቱ ኖርዌይ ከሃምሳ ሺህ ትንሽ በላይ ልጆች ይወለዳሉ።
- በኖርዌይ ያሉ ሴቶች በአማካይ እያንዳንዳቸው 1,4 ልጆች ይወልዳሉ (2023)።
ምንጭ፦ SSB/ስታቲስቲክስ ኖርዌይ
የተለያዩ የቤተሰብ አይነቶች
ብዙ ሰዎች የአንድ ቤተሰብ አካል ናቸው። አንዳንዶቹ ከሌሎች የቤተሰብ አባላት ጋር ይኖራሉ፡ ሌሎች ደግሞ ብቻቸውን ይኖራሉ። ለብቻቸው የሚኖሩ ሰዎች ብዙ ጊዜ ቤተሰብ አላቸው፡ ነገር ግን፡ ቤተሰባቸው በሌላ ቤት፡ በሌላ ከተማ ወይም በሌላ አገር ሊኖሩ ይችላል።
ቤተሰብ በአንድ ቤት ውስጥ የሚኖሩ ገንዘባቸውን በአንድነት የሚጠቀሙ ሰዎችን የቀፈ ነው:: አንድ ቤተሰብ፡ በኣንድ ወይም ከዚኣ በላይ ሊያካትት ይችላል። በኖርዌይ፡ በአማካይ በአንድ ቤት ውስጥ ከሁለት በላይ ሰው ይኖራሉ።
በኖርዌይ የሚኖሩ የተለያዩ የቤተሰብ አይነቶች ማሳያ ሊሆኑን የሚችሉትን ምሳሌዎች ከታች እንመለከታለን። (1)ላጤ፡ ያላገባ/ያላገባች፣ (2)ወላጆችና ልጆቻቸውን፣ (3)እናትና ልጆቿን ብቻ፣ (4)ሚስት፡ ኣጋር/ ሳይጋቡ ኣብረው የሚኖሩ፣ (5)ባለትዳሮችህ ወይ ሳይጋቡ ኣብሮ ነዋሪ።
ጋብቻ
በኖርዌይ በየአመቱ በግምት 20ሺ ጥንዶች ጋብቻ ይፈጸማሉ። ጋብቻ ለመፈጸም ከ18 አመት በላይ መሆንና በፈቃደኝነት ላይ የሚመሰረት ሊሆን ይገባዋል፡፡ በኖርዌይ ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ ሁለት የተመሳሳይ ጾታ ሰዎች ጋብቻ መፈጸም የሚችሉበት ሕጋዊ ፈቃድ ተሰጥቷል፡፡ ተጋብታችሁ የምትኖሩ ከሆነ ለኑሮ የሚሆን አቅርቦት ከሁለታችሁም ይጠበቃል፡፡ በጋራ ብድር የሚወስዱ ባለትዳሮች ሁለቱም ለዚህ ብድር ተጠያቂ ናቸው። የሚገዙትንም የትኛውንም ነገር አንድ ላይ ያዙዋቸው፡፡ ይህ አሰራር: አንዱ አካል ብቻ ከቤት ውጪ የሚሰራ ቢሆንም ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ ከ ጥር 1 ቀን 2020 በኖርዌይ የተወለዱ ልጆች ወላጆች፡ በመሠረቱ የጋራ የወላጅ ኃላፊነት አለባቸው። ይህ የተጋቡ፣ አብረው የሚኖሩ ወይም አብረው የማይኖሩ ወላጆችን ይመለከታል።
ጋብቻ ከፈጸሙ ጥንዶች መሃል በግምት 40 ከመቶ የሚሆኑቱ፣ ብዙም ሳይቆዩ ፍቺ ይፈጽማሉ። የፍቺ ጥያቄ አቅራቢው ከሁለቱ ወገኖች አንዱ ወንዶች አሊያም ሴቶቹ ሊሆኑ ይችላሉ።ይህንን ለመፈጸም ዋናው ሕግ የፍቺ ጥያቄ ከማቅረባችሁ ከአንድ አመት አስቀድማችሁ ተለያይታችሁ ልትኖሩ ይገባል የሚል ነው። ጋብቻው በግዳጅ የተፈጸመ ከሆነ አሊያም በተደጋጋሚ ጸብ የሚፈጠርበት ከሆነ ግን ፍቺው ወዲያውኑ ይፈጸማል።
75 ከመቶ የሚሆኑት ልጆች ከእናት እና ከአባታቸው ጋር ይኖራሉ። ከፍቺ በኋላ እናትና አባት ልጆቻቸውን የመንከባከብ መብት እና ግዴታ አለባቸው።
ብዙዎች ሰዎች ከጋብቻ በፊት ጥቂት ጊዜ አብረው መኖርን ይመርጣሉ። ሳይጋቡ በአንድነት አብረው የሚኖሩ ጥንዶች የጋራ የሆኑ የገንዘብ እንዲሁም ሌሎች ህጋዊ መብቶችን ሊተገበሩላቸው አይችሉም። አብዛኛዎቹ ሰዎች አብረው መኖራቸውን ሲያቆሙ የውርስ ወይንም የሃብት ክፍፍል ስምምነቶችን ለማድረግ ወደ ጠበቃ ይሄዳሉ።
ኣብራችሁ ተወያዩ
- ቤተሰብ ምንድነው?
- እስቲ በተለያየ መንገድ አብሮ ስለሚኖርባቸው መንገዶች ተነጋገሩ።
- በኖርዌይ እና በትውልድ አገራችሁ መካከል ያለውን የቤተሰብ መጠን ልዩነት ስለተለያዩ ማህበረሰቦች ምን አይነት ነገር ያሳያችኋል? በሰዎች ሕይወት በማሕበራዊም ምጣኔያዊም ላይ ምን የሚያስከትለው ነገር አለ?
- እስቲ ፍቺ የፈጸሙ ወላጆች ልጆቻቸውን በጥሩ ሁኔታ ሊንከባከቡ ስለሚችሉበት ጥሩ መንገድ ተወያዩበት።
- ብዙ ሰዎች ተጋብቶ ከመኖር ይልቅ ያለጋብቻ አብረው መኖርን የሚመርጡት ለምን እንደሆነ ተወያዩበት።
ኣና እና ሞርተን የተጋቡ ጥንዶች ሲሆኑ ሁለት ወጣት ልጆች አሏቸው። ልጆቻቸው መዋዕለ ሕጻናት የገቡ ሲሆን ኣናና ሞርተን ደግሞ የሙሉ ጊዜ ሠራተኞች ናቸው። በኣና ቤተሰቦች መኖሪያ አቅራቢያም መኖሪያ ቤት ገዝተዋል። ቤቱ ውድ በመሆኑ ምክንያት ቤቱን የገዙበትን ገንዘብ ያገኙት በብድር ነበር። ሁለቱም የትምህርት ቤት ክፍያ የከፈሉበትና እና መኪና የገዙበት ዕዳ አለባቸው። በጣም ታክቷቸዋል። የቤቱን ሥራ ማን መሥራት እንዳለበት እንዲሁም፣ ይህ ጉዳይ አንዴት መቋጨት እንዳለበት ይከራከራሉ። በጣም በሚጨቃጨቁበት ጊዜም ኣና “ይህን ሁኔታ ከዚህ በላይ መቋቋም አልችልም ፍቺ እፈልጋለሁ” ብላ ታምባርቅበታለች።
- እስቲ ስለ ኣናና ሞርተን ሁኔታ ተነጋገሩ። የዕለት ተዕለት ኑሮአቸውን ቀላል ይሆን ዘንድ ምን ማድረግ ይችላሉ?
- ኣናና ሞርተን ፍቺ ለማድረግ ቢወስኑ ለቤተሰቡ ምን አይነት መዘዝ ይዞ ይመጣል?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ቤተሰብ ምን ማለት ነው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
በአንድ የኖርዌጅያን ቤተሰብ ውስጥ በአማካይ ምን ያክል ሰዎች ይኖራሉ?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
የተጋቡ ጥንዶች ልጆች በሚኖራቸው ጊዜ የወላጃዊ ሃላፊነቱ የማን ይሆናል?
ትክክል ወይም ስሕተት የሆነውን ይምረጡ፡፡
መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው ?
ትክክል ወይም ስሕተት የሆነውን ይምረጡ፡፡
መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው ?