የጥርስ ጤንነት
ፊልሙን ይመልከቱ
የጥርስ ጤንነት
- ልጆች እና ወጣቶች 18 ዓመት እስኪሞላቸው ድረስ፡ በመንግስት የጥርስ ሕክምና አገልግሎት መደበኛ የጥርስ ምርመራ ያደርጋሉ። እነዚህ ምርመራዎች የሚሸፈነው በመንግስት ነው።
- ዕድሜያቸው ከ18-24 የሆኑ ሰዎች 25 በመቶ የጥርስ ህክምና ወጪ በመንግስት የጥርስ ሕክምና አገልግሎት የሚከፍሉ ሲሆን መንግስት ቀሪውን 75 በመቶ ይሸፍናል።
- ከዚህ ውጪ ያሉ አዋቂዎች ለጥርስ ህክምና ሙሉ ዋጋ ይከፍላሉ።
- አዋቂዎች ከግል የጥርስ ሐኪም ጋር የራሳቸውን ቀጠሮ መያዝ አለባቸው። በዓመት አንድ ጊዜ ምርመራ ማድረግ የተለመደ ነው።
- አንድ ልጅ ወይም ወጣት የጥርስ 'ማስተካከያ ብሬስ' ለማሰር የሚያስፈልጋቸው ከሆነ፡ ወላጆቻቸው ወጪውን መሸፈን ኣለባቸው።
የልጆች የጥርስ ጤንነት
ወላጆች ለልጆቻቸው የጥርስ ጤንነት ተጠያቂ ናቸው። ስኳር ለጥርሶች ጎጂ ነው። ኣብዛኛው የምንበላው እና የምንጠጣው ነገሮች፣ ለምሳሌ፡ ቸኮሌት፡ ብስኩት፡ ለስላሳ መጠጦች፡ ማርማላት፡ ስኳሽ, ኬኮች እና ጣፋጮች ስኳር ይይዛሉ። ስለሆነም፡ ሁሉም ሰው በቀን ሁለት ጊዜ፡ ጥዋት እና ማታ፡ ጥርሱን መቦረሽ አለበት። ደካማ የወተት ጥርሶች አዲስ ለሚተኩ ጥርሶች ደካማ እንዲሆኑ ሰበብ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ፡ የልጆችን ጥርስ፡ ከልጅነታቸው ጀምሮ መንከባከብ አስፈላጊ ነው።
ኣብራችሁ ተወያዩ
- ጥሩ የጥርስ ጤና ምን እንደሆነ ተወያዩበት።
- ምን ያህል ጊዜ ወደ ጥርስ ሀኪም መሄድ አስፈላጊ ነው ብለው ያስባሉ?
- በአመጋገብ እና በጥርስ ጤና መካከል ያለውን ግንኙነት ተወያዩበት።
- መንግስት ለህጻናት የጥርስ ህክምና ክፍያ ይሸፍናል፡ ለአዋቂዎች ባለመሸፈኑ ምን ያስባሉ?
- በኖርዌይ፡ ልጆች የወተት ጥርሳቸው ሲነቀሉ፡ በአንድ ብርጭቆ ውስጥ ያስቀምጧቸዋል። የጥርስ ተረት ‘ታንፌን’ በሌሊት መጥታ በብርጭቆው ውስጥ ገንዘብ ታስቀምጣለች። እንዲህ ያለ የባህል ልማዶች እንዳሉ ያውቃሉ?
አረፍተ ነገሩን አሟሉ
ልጆች እና ወጣት ሰዎች እድሜያቸው ……እስኪሆን ድረስ ቋሚ የሆነ የጥርስ ምርመራ ይደረግላቸዋል፡፡
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ጥርሳችሁን በቀን ምን ያክል ጊዜ ትቦርሻላችሁ?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ለጥርስ የሕክምና አገልግሎት ሙሉ ክፍያውን የሚከፍለው ማነው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 24 የሆኑ ወጣቶች ለጥርስ ሕክምና ምን ያህል ይከፍላሉ?
ትክክል ወይም ስህተት ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?
ምስሉን ተጫኑት፡፡
መንግስት፣ 75 ከመቶ የሚሆነውን የጥርስ ሕክምና ወጪ የሚሸፍኑት ስንት አመት ለሆናቸው ልጆች ነው?