ቀደምት ኖርዌጃውያን
ቀደምት ኖርዌጃውያን
የበረዶው ዘመን
ከረጅም ጊዜ በፊት፡ የአውሮፓ ሰሜናዊ ክፍል እስከ 3,000 ሜትር ጥልቀት ባለው የበረዶ ሽፋን ተሸፍኖ ነበር። የሙቀት መጠኑ ቀስ በቀስ መጨመር ስለ ጀመረ፡ በረዶው ቀስ በቀስ መቅለጥ ጀመረ።
የድንጋይ ዘመን (10,000 ዓመተ ዓለም–2,000 ዓ.ዓ)
የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ወደ ኖርዌይ የመጡት ከ12,000 ዓመታት በፊት አካባቢ ነው። በዋናው አውሮፓ እና በኖርዌይ የባህር ጠረፍ መካከል ያለውን ቦታ በረዶ ሸፍኖት ነበር፣ስለሆነም፡ ሰዎች እና እንስሳት በበረዶ ተሻግረው ወደ ኖርዌይ እንደመጡ ይታመናል። የአርኪኦሎጂ ግኝቶች እንደሚያመለክቱት ሰዎች በቤሪ፣ እንጉዳይ እና በተያዙት አሳ እና እንስሳት ላይ ይኖሩ ነበር። ከድንጋይ፣ ከአጥንትና ከእንጨት የተሠሩ መሳሪያዎችን እንደ የጦር መሣሪያዎችን ይጠቀሙ ነበር። ለዚህ ነው፡ ይህ ክፍለ ዘመን የድንጋይ ዘመን በመባል፣ የሚታወቀው።
በኖርዌይ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች እርሻ የጀመሩት ከ4,000 አመታት በፊት ነው፡፡
የነሐስ ዘመን (1,800 ዓ.ዓ –500 ዓ.ዓ)
ባለጠጋ የሆኑ ገበሬዎች፡ ቀስ በቀስ፡ በነሃስ ቁስቁሶች፡ የጦር መሳሪያዎችና፡ ጌጣጌጦችን መሥራት ችለዋል፡፡ ገበሬዎች ፈረሶችን ለእርሻ መጠቀም ጀመሩ፡ ሴቶች ደግሞ ከበግ ጸጉር ፈትል በመፍተል ልብሶችን መሥራት ጀመሩ፡፡
ይህንን ክፍለ ዘመን የነሃስ ዘመን በማለት ይጠራል፡፡ በነሃስ ዘመን የነበረው የኖርዌይ የአየር ጠባይ አሁን ካለው የአየር ጠባይ ይልቅ የሚሞቅ ነበር፡፡
የብረት ዘመን (500 ዓ.ዓ–1050 ዓ.ም.)
በዚህ ወቅት የነበረው የአየር ንብረት ዛሬ በኖርዌይ ካለው የአየር ንብረት ጋር ተመሳሳይ ነበር። በኖርዌይ ይኖሩ የነበሩት ሰዎች እርጥበት ኣዘሉ (ማርሽላንድ) ውስጥ ካገኙት የብረት ማዕድን፡ በማቅለጥ ብረት እንዴት እንደሚሠሩ ተምረዋል እና መሳሪያዎችን እና የጦር መሳሪያዎችን ለመሥራት ይጠቀሙበት ነበር። እነዚህ መሳሪያዎች መሬቱን ለማረስ ቀላል አድርገውላቸዋል፡ ስለዚህ ምግብም በብዛት ማምረት ቻሉ። የሕዝቡ ቁጥርም ጨመረ። ይህንን ዘመን፡ የብረት ዘመን ተብሎ ይጠራል።
የቫይኪን ዘመን (800 -1050 ዓ.ም.)
በጣም ሀብታም እና ኃያላን ገበሬዎች በትልልቅ እርሻዎች ላይ ይኖሩ ነበር። እንኚህ ገበሬዎች፡ አለቃ ተብለው ይጠሩ ነበር። ምድራቸውን የሚከላከሉ ወታደሮች ነበሯቸው። በ8 ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ፡ ከእነዚህ አለቆች መካከል አንዳንዶቹ ኖርዌይን ለቀው ወደ ሌሎች የአውሮፓ አገሮች ሄዱ። አንዳንዶቹ ብቁ ነጋዴዎች እንኳን ቢኖሩ፡ ጦርነት እየከፈቱ ዘርፈዋል። እነኚህ ቫይኪንጎች ተብለው ይጠሩ ነበር።
በ872 ዓ.ም. የቫይኪንግ ሃራልድ ፋይርሃይር፡ የመላ ኖርዌይ ንጉሥ ሆነ።
የቫይኪንጎች ሃይማኖት ከኖርስ አማልክቶች ተረቶች በተያያዘ፡ ጥሩ የእርሻ ምርት፡ በፍሬያማነትና በጦርነት እንደሚረዳ የሚያካትት እምነት ነበራቸው። አንዳንድ ቫይኪንጎች በአውሮጳ በሚያደርጉት ጉዞ ግን ከክርስትና ሃይማንት ጋር ግንኙነት ስለፈጠሩ፡ እምነቱን ወደ ኖርዌይ ይዘው መጡ። ስለሆነም፡ ክርስትና ወደ ኖርዌይ የገባው በ11ኛው ክፍለ ዘመን ነው። 1030 ዓ.ም. ግን በኖርዌይ ታሪክ ውስጥ የሚታወስ ነው። በዚሁ ግዜ፡ ከትሮንዴሃይም ኣጠገብ፡ በስቲክልስታድ ጦርነት የተካሄደበት ወቅት ነበር። ክርስቲያን የሆነው ኦላቭ ሃራልድሰን፡ በአሮጌው የቫይኪንግ ሃይማኖት ተከታይ ከሆኑት፡ በጣም ሃያላን ኣለቆች ጋር ተዋግቶ ተሸነፈ። ክርስትያኑ ኦላቭ በጦርነቱ ቢሸነፍም፡ የክርስትና ሃይማኖት በኖርዌይ፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቶ፡ ቀስ በቀስ የድሮውን የኖርስ ሃይማኖት ተክቷል።
ኣብራችሁ ተወያዩ
- የትውልድ ሃገርህን የመጀመሪያ ታሪክ ታውቃለህ?
- በኖርዌይ መጀመሪያ ዘመን የተከሰተውን ታሪክ፡ በአገርዎ በተመሳሳይ ጊዜ ከተፈጠረው ጋር ማወዳደር ይችላሉ?
ወደ ኖርዌይ ከመምጣትዎ በፊት ስለ ቫይኪንጎች ሰምተው ያውቃሉ?- ቫይኪንጎች በትውልድ ሀገርዎ ታሪክ ላይ ምንም ተጽእኖ ነበራቸው?
- ሰዎች አንድን ሃይማኖት እንዴትና ለምን አጥፍተው በሌላው ሊተኩ እንደሚችሉ ተነጋገሩ፡፡ይህ በሰዎች ሕይወት ላይ ምን ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል? በትውልድ ሀገርዎ ተመሳሳይ ነገር ተከስቷል?"
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
የመጀመሪያዎቹ ነዋሪዎች ወደ ኖርዌይ የደረሱት መቼ ነበር?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
በነሃስ ዘመን በኖርዌይ ምን ተፈጠረ?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
በየትኛው ክፍለዘመን ነበር ዛሬ ላይ የነበረው አይነት የአየር ጠባይ፡ አሁን ካለው የኖርዌይ የአየር ጠባይ ጋር ተመሳሳይ የነበረው?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ። ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ። ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?
ትክክለኛውን ምስል ይምረጡ፡፡
የትኛው ምስል ነው የቫይኪንጎችን ዘመን የሚገልጸው?
ምስሉን ለመክፈት ተጫኑት፡፡
የዘመን ቅደም ተከተልን የሚገልጸውን ትክክለኛ ምስል ተጫኑት፡፡ የብረት ዘመን የቱ ነበር?
ምስሉን ለመክፈት ተጫኑት፡፡
የትኛው ምስል ነው የቫይኪንጎችን ዘመን የሚገልጸው?
ምስሉን ለመክፈት ተጫኑት፡፡
በጊዜ መስመር ውስጥ፡ ትክክለኛውን ክፍለ ጊዜ፡ ተጫኑ። የነሐስ ዘመን መቼ ነበር?"