የሴት ልጅ ግርዛት
የሴት ልጅ ግርዛት
የሴት ልጅ ግርዛት ማለት ያለምንም ጥቅም ወይንም አሳማኝ ምክንያት የሴት ልጅን ብልት ውጪያዊ አካል መጉዳት ወይንም ማስወገድ ነው። የሴት ልጅ ግርዛት በሴት ላይ የሚያደርሰውን የጉዳት መጠን ከግምት ውስጥ ያላሰገባ እርምጃ ነው። በኖርዌይ ውስጥ የሴት ልጅ ግርዛት ሕገወጥ ተግባር ነው። የሴት ልጅ ግርዛት ጎጂ እና ቀሪውን ሕይወቷን የሚጎዳ ተግባር ነው።
በኖርዌጃውያን ሕብረተሰብ ውስጥ የጾታ እኩልነት በጣም ኣስፈላጊ እሴት ነው። ማንኛውም ሰው በራሱ ሰውነት ላይ የመወሰን መብት አለው። ስለሆነም፡ የሴት ልጅ ግርዛት ይህንን መብት የሚጋፋ ድርጊት ነው። ዓለምአቀፉዊ ስምምነትንም የሚጥስ ነው። ይህ ድርጊት በሚፈጸምባቸው አንዳንድ አገራትም ውስጥ ይህ ድርጊት በሕገወጥነት ተፈርጇል፡፡
- የሴት ልጅን ወይም የሴትን ብልት ለመጉዳት ሆን ብሎ መጉዳት ህገወጥ ነው።
- የሴት ልጅን ብልት የሚጎዳ ነገር ከሚያደርጉ አካላት ተባብሮ መገኘት በራሱ ሕገወጥ ተግባር ነው።
- ሴት ልጆችን ከኖርዌይ ውጪ ወደሌላ አገር ወስዶ ብልቷ ላይ ጉዳት ማድረስ ሕገወጥ ተግባር ነው፡፡
- የምትገረዘው ሴት በግርዛቱ ብትስማማም አንኳ ድርጊቱ ሕገወጥ ነው።
- እንዲሁም፡ ቀድሞ ግርዛት የተፈጸማበቸው የሴቶች አካል ወደነበረበት መመለስ አሊያም መልሶ ለማስተካከል መሞከር ሕገወጥ ድርጊት ነው።
- ህጉን በመጣስ ቅጣቱ እስከ ስድስት ዓመት የሚደርስ እስራት ነው።
- ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትል የሴት ልጅ ግርዛት ተፈጽሞ ከሆነ፡ ደግሞ እስከ 15 አመት በሚደርስ እሥራት ያስቀጣል።
- በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ላይ የሚገኙ ባለሙያዎች እንዲሁም ሃይማኖታዊ የሕብረተሰብ ክፍሎች የሴት ልጅ ግርዛትን ለማስቀረት የመምከር ኃላፊነት አለባቸው፡፡ ይህን አለማድረግ የማስቀረት ግዴታን መጣስ ሲሆን እስከ አንድ አመት በሚደርስ እስራት ይቀጣል።
ምንጭ፡ Lovdata
ለግርዛት የተጋለጠች ወይም የግርዛት ስጋት ያለባት ሴት፡ ከሚከተሉት ውስጥ እርዳታ መጠየቅ ትችላለች፡-
- መደበኛ ሓኪም
- የጤና ማዕከል
- ፖሊስ
- የግዳጅ ጋብቻን ለማስቆም የተቋቋሙ የባለሙያዎች ቡድን፣ የሴት ልጅ ግርዛት እና አሉታዊ ሕብረተሰባዊ ቁጥጥር፣ ስልክ ቁጥር 478 090 50
- የቀይ መስቀል የእርዳታ መስመር 815 55 201
- ከኖርዌይ ውጪ ከሆናችሁ ደግሞ የኖርዌይን ኤምባሲ ማናገር ትችላላችሁ።
ኣብራችሁ ተወያዩ
- በአንዳንድ ባህሎች ሴት ልጆችን የመገረዝ ባህል ለምን አለ?
- ይህንን ባህል ለማጥፋት የተለያዩ ቡድኖች ምን ሊያደርጉ ይችላሉ?
- በኖርዌይ ያለው ጥብቅ ሕግ ልጃገረዶች እንዳይገረዙ እንዴት ይከላከላል?"
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
የሴት ልጅ ግርዛት ምን ማለት ነው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
በተባባሰ የሴት ልጅ ግርዛት ምክንያት የስንት አመት እስራት ልትቀጣ ትችላለህ?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
የሴት ልጅ ግርዛት ተግባር ተባባሪ ሆኖ መገኘት እስከ ስንት አመት ያሳስራል?
አረፍተ ነገሩን አሟሉ፡፡
አንዲት ልጃገረድ ወይንም ሴት ለግርዛት ከተስማማች ግርዛቱ…………ይሆናል