የልጆች ደህንነት አገልግሎት
የልጆች ደህንነት አገልግሎት
ልጆችን መንከባከብና ማሳደግ የወላጆች ተቀዳሚ ኃላፊነት ነው። አንዳንድ ወላጆች ለአጭር አሊያም ለረጅም ጊዜ ድጋፍ ሊፈልጉ ይችላሉ፤ለምሳሌ በአስቸጋሪ የሕይወት ሁኔታ ውስጥ እያለፉ ሊሆን ይችላል አሊያም ሌሎች ምክንያቶች ሊኖሯቸው ይችላሉ። የልጆች ደህንነት አገልግሎት በዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ የሚያልፉ ልጆችንና ወላጆችን ይደግፋል። በኖርዌይ የሚገኝ ማንኛውም ማዘጋጃ ቤት ይህንን አይነት የሕጻናት ደህንነት ድርጅቶች አሏቸው።
የልጆች ደህንነት ኣገልግሎት ታሪክ ወደኋላ ተጉዞ እ.ኤ.አ ከ19ኛው ክፍለ ዘመን ይጀምራል። ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ተጨማሪ ድጋፍና ከለላ የሚፈልጉ ልጆችን የሚረዳ ድርጅት በማቋቋም ኖርዌይ ከዓለም ቀዳሚዋ አገር ናት። የመጀመሪያው ድርጅት “ቬርግራደስሎቨን” (የልጆች ደህንነት ኣገልግሎት ሕጋዊ ድንጋጌ) ወደ ሥራ የገባው እ.ኤ.አ በ1900 ነበር።
የልጆች የደህንነት አገልግሎት የእርዳታ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ልጆች ድጋፍ የሚያደርግ ድርጅት ነው።
- የልጆች ደህንነት ኣገልግሎት፡ የልጆች እና በአፍላ ወጣትነት (በጉርምስና) እድሜ ላይ ያሉ ልጆች ደህንነቱ የተጠበቀ የልጅነት ጊዜ ማሳለፍ እንዲችሉ ደሕንነታቸውን ያረጋግጣል።
የልጆች የደሕንነት ኣገልግሎት፣ ለልጆች፡ በአፍላ የወጣትንነት እድሜ ላይ ላሉት ልጆች እና ለቤተሰቦቻቸው አርዳታ እና ድጋፍ ያደርጋል። - የልጆች የደህንነት ኣገልግሎት፡ የተለያዩ የድጋፍ አገልግሎቶችን፣ ማለትም የምክር፡ የእረፍትና ግዜና የግል ድጋፍን ይሰጣል። ወላጆችም ይህንን አይነት የድጋፍ ይደረግልን ጥያቄ ማቅረብ ይችላሉ።
- የልጆች የደህንነት አገልግሎት ዋና ሥራው፡ ለልጆች፣ ከተቻለ ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ፡ ከለላ መስጠት ነው።
- አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ፡ የልጆች ደህንነት አገልግሎት፣ ከወላጆቻቸው ጥበቃ ለሚፈልጉ ልጆች አዲስ ቤተሰብ ማግኘት ነው።
- ማንኛውም፡ በልጆች ደህንነት አገልግሎት ውስጥ የሚሠራ ሰው፡ ሚስጥር የመጠበቅ ግዴታ አለበት።
- ከልጆቹ ጋር የሚሰራ ማንኛውም ሰው፡ በቤት ውስጥ ግጭት መኖሩን ካወቀ፡ ለልጆች ደሕንነት አገልግሎት ጽሕፈት ቤት የማሳወቅ ግዴታ/ ኃላፊነት አለበት።
- ማንኛውም ሰው አንድን ልጅ በተመለከተ የሚያሳስበው ነገር ካለ፡ ለልጆች ደህንነት አገልግሎት ማሳወቅ ኣለበት።
ሕጻናትና አዋቂዎች የልጆች፡ የደህንነት አገልሎትን እንዴት ማግኘት ይችላሉ?
ሁሉም የኣከባቢ ኣስተዳድሮች የልጆች ደህንነት አገልግሎት ቢሮዎች ያሏቸው ሲሆን ሁልጊዜ በሥራ ሰአት አገልግሎት ይሰጣሉ። ልጆችም ሆኑ አዋቂዎች ይህንን ቢሮ በቀጥታ ማግኘት ይችላሉ። በምሽት ወይንም በእኩለ ሌሊት ልጆች፡ አሊያም በልጆች ጉዳይ ስጋት የገባው ማንኛውም ሰው በ116 111 የድንገተኛ መስመሮች በመደወል ለልጆችና ለወጣቶች አገልግሎት ማግኘት ይችላል።
ኣብራችሁ ተወያዩ
- በኖርዌይ ማህበረሰብ መካከል የልጆች የደህንነት አገልግሎትን ሚና በተመለከተ ተወያዩ።
- ልጆች ከራሳቸው ቤተሰብ ጥበቃ የሚደረግላቸው በምን አይነት መንገድ ነው?
- በቅርቡ ኖርዌይ መጥተው መኖር የጀመሩ ሰዎች፡ በልጆች የደህንነት አገልግሎት ላይ እምነት የላቸውም። ይህ የሆነው ለም ይመስላችኋል?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
የኖርዌይ የመጀመሪያው የህፃናት ደህንነት ሕግ (Vergerådsloven) መቼ ተግባራዊ ሆነ?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
የሕጻናት ደህንነት አገልግሎት ሰራተኞችን የት ልታገኟቸው ትችላላችሁ?
ኣረፍተ ነገሩን ኣሟላ
ከልጆች ጋር የሚሰራ ማንኛውም ሰው በ……………ላይ ጥርጣሬ ሲኖረው የማሳወቅ ሃላፊነት አለበት፡፡
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?